1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

حديث ከእነዚህ ሴት ልጆች አንዳችን ሃላፊነት ወስዶ ለነርሱ መልካምን ላደረገ እነርሱ ለርሱ የእሳት ግርዶሽ ይሆኑለታል።

عَن عَائِشَةَ أُمِّ المؤْمِنين رضي الله عنها زَوْجَ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ حَدَّثَتْهُ قَالَتْ:
جَاءَتْنِي امْرَأَةٌ مَعَهَا ابْنَتَانِ تَسْأَلُنِي، فَلَمْ تَجِدْ عِنْدِي غَيْرَ تَمْرَةٍ وَاحِدَةٍ، فَأَعْطَيْتُهَا فَقَسَمَتْهَا بَيْنَ ابْنَتَيْهَا، ثُمَّ قَامَتْ فَخَرَجَتْ، فَدَخَلَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَحَدَّثْتُهُ، فَقَالَ: «مَنْ يَلِي مِنْ هَذِهِ البَنَاتِ شَيْئًا، فَأَحْسَنَ إِلَيْهِنَّ، كُنَّ لَهُ سِتْرًا مِنَ النَّارِ».

የአማኞች እናትና የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባለቤት ከሆነችው ከዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች:
«ሁለት ሴት ልጆች ያሏት አንዲት ሴት ልትለምነኝ መጣች። እኔ ዘንድም ከአንድ ተምር ውጪ አላገኘችም። እርሱንም ስሰጣት ለሁለት ሴት ልጆቿ ሁለት ቦታ ከፋፍላ ሰጠች። ከዚያም ተነስታ ሄደች። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እኔ ዘንድ ሲገቡ ሁኔታውን ነገርኳቸው። እርሳቸውም እንዲህ አሉ: "ከእነዚህ ሴት ልጆች አንዳችን ሃላፊነት ወስዶ ለነርሱ መልካምን ላደረገ እነርሱ ለርሱ የእሳት ግርዶሽ ይሆኑለታል።"»

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5995

المعنى الإجمالي

የአማኞች እናት የሆነችው ዓኢሻ (አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና) እንዲህ በማለት ተናገረች: ሁለት ሴት ልጆች ያሏት አንዲት ሴት እነርሱን ይዛ የሚበላ ነገር እንድትሰጣት ልትለምናት መጣች። ዓኢሻም ከአንድ ተምር ውጪ አላገኘችም። እርሱንም ስትሰጣት ለራሷ ምንም ሳትበላ ለሁለት ሴት ልጆቿ ሁለት ቦታ ከፋፍላ ሰጠች። ከዚያም ተነስታ ሄደች። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እርሷ ዘንድ ሲገቡ ሁኔታውን ነገረቻቸው። እርሳቸውም እንዲህ አሉ: "ከእነዚህ ሴት ልጆች አንዳችን ሃላፊነት ወስዶ ለነርሱ መልካምን ያደረገ፣ በስነስርዓት ያነፃቸው፣ ያለበሳቸውና በዚህም ላይ የታገሰ እነርሱ ለርሱ የእሳት ግርዶሽ ይሆኑለታል።"

من فوائد الحديث

  1. ሴቶችን መንከባከብና ለነርሱ መልካም ለማድረግ መልፋት ከእሳት የሚያርቁ ከሆኑት በላጭ መልካም ስራዎች መካከል አንዱ ነው።
  2. የሰው ልጅ ትንሽ ብትሆን እንኳ በሚችለው መመፅወቱ እንደሚወደድለት እንረዳለን።
  3. ወላጆች ለልጆቻቸው ያላቸውን የጠና ርህራሄ እንመለከታለን።
  4. የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቤቶች የነበራቸውን ሁኔታ ተገልጾ እናየዋለን። የርሳቸው ሲሳይ ለቤተሰባቸው ብቻ የሚበቃ ነበር።
  5. ሌላውን ማስቀደም ያለው ደረጃ መገለፁ። ይህ ባህሪ የአማኞች ባህሪ ነው። ዓኢሻ (አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና) ይህቺን ሴትና ልጆቿን ከራሷ በላይ አስቀደመቻቸው። ይህም ተምሩን በዚህ ደረጃ በጣም እየፈለገችውም መስጠቷ የርሷን ቸርነትና ደግንት ይጠቁማል።
  6. ሴቶችን መውለድ ፈተና ተብሎ የተጠራው እነርሱን ማሳደግ አድካሚና ከባድ ስለሆነ ወይም አንዳንድ ሰዎች ሴት ሲወለድ ስለሚጠሉ ወይም በብዛት ለነርሱ የሚሆን የገቢ ምንጭና መተዳደሪያ ስለማይገኝ ነው።
  7. እስልምና የተወገዘ የድንቁርና ዘመን ባህልን ከስሩ መናዳቸውን እንረዳለን። ከነዚህም መካከል አንዱ ሴቶችን በመንከባከብ አደራ ማለቱ ነው።
  8. በሌሎች ዘገባዎች እንደመጣው አንዲት ሴት ልጅ ብቻ እንኳ ብትሆን ይህ ሐዲሡ ላይ የተጠቀሰውን ምንዳ ታስገኛለች።

عرض الترجمات

36 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية