1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

حديث አልሏሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነልዐጅዚ ወልከሰሊ ወልጁብኒ ወልቡኽሊ ወልሀረሚ ወዐዛቢል ቀብር ፤ አልሏሁምመ አቲ ነፍሲ ተቅዋሃ ወዘክኪሃ አንተ ኸይሩ መን ዘክካሃ፤ አንተ ወሊይዩሃ ወመውላሃ፤ አልሏሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚን ዒልሚን ላ የንፈዑ፤ ወሚን ቀልቢን ላ የኽሸዑ፤ ወሚን ነፍሲን ላ ተሽበዑ፤ ወሚን ደዕወቲን ላ ዩስተጃቡ ለሃ።" (ትርጉሙም፡ "አላህ ሆይ! እኔ ከስንፍና ፣ ከመታከት ፣ ከፈሪነት ፣ ከስስት ፣ ከመጃጀትና ከቀብር ቅጣት ባንተ እጠበቃለሁ። አላህ ሆይ! ለነፍሴ ፍራቻዋን ስጣት፤ ነፍሴን ለማጥራት የተሻልከው አንተው ነህና ነፍሴን አጥራት፤ አንተ ረዳቷና ተቆጣጣሪዋ ነህና። አላህ ሆይ! እኔ ከማይጠቅም ዕውቀት፣ አንተን ከማይፈራ ልብ፣ ከማትጠግብ ነፍስ፣ ተቀባይነት ከሌላት ዱዓም ባንተ እጠበቃለሁ።")

عَنْ زَيْدِ بْنِ أَرْقَمَ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ: لَا أَقُولُ لَكُمْ إِلَّا كَمَا كَانَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ: كَانَ يَقُولُ:
«اللهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْعَجْزِ وَالْكَسَلِ وَالْجُبْنِ وَالْبُخْلِ وَالْهَرَمِ وَعَذَابِ الْقَبْرِ، اللهُمَّ آتِ نَفْسِي تَقْوَاهَا، وَزَكِّهَا أَنْتَ خَيْرُ مَنْ زَكَّاهَا، أَنْتَ وَلِيُّهَا وَمَوْلَاهَا، اللهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنْ عِلْمٍ لَا يَنْفَعُ، وَمِنْ قَلْبٍ لَا يَخْشَعُ، وَمِنْ نَفْسٍ لَا تَشْبَعُ، وَمِنْ دَعْوَةٍ لَا يُسْتَجَابُ لَهَا».

ከዘይድ ቢን አርቀም - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «እኔ የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ይሉ ከነበሩት ውጪ አልልም። እርሳቸው እንዲህ ይሉ ነበር:
"አልሏሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነልዐጅዚ ወልከሰሊ ወልጁብኒ ወልቡኽሊ ወልሀረሚ ወዐዛቢል ቀብር ፤ አልሏሁምመ አቲ ነፍሲ ተቅዋሃ ወዘክኪሃ አንተ ኸይሩ መን ዘክካሃ፤ አንተ ወሊይዩሃ ወመውላሃ፤ አልሏሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚን ዒልሚን ላ የንፈዑ፤ ወሚን ቀልቢን ላ የኽሸዑ፤ ወሚን ነፍሲን ላ ተሽበዑ፤ ወሚን ደዕወቲን ላ ዩስተጃቡ ለሃ።" (ትርጉሙም፡ "አላህ ሆይ! እኔ ከስንፍና ፣ ከመታከት ፣ ከፈሪነት ፣ ከስስት ፣ ከመጃጀትና ከቀብር ቅጣት ባንተ እጠበቃለሁ። አላህ ሆይ! ለነፍሴ ፍራቻዋን ስጣት፤ ነፍሴን ለማጥራት የተሻልከው አንተው ነህና ነፍሴን አጥራት፤ አንተ ረዳቷና ተቆጣጣሪዋ ነህና። አላህ ሆይ! እኔ ከማይጠቅም ዕውቀት፣ አንተን ከማይፈራ ልብ፣ ከማትጠግብ ነፍስ፣ ተቀባይነት ከሌላት ዱዓም ባንተ እጠበቃለሁ።")

ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ ሙስሊም - 2722

المعنى الإجمالي

ከነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዱዓ መካከል "አላህ ሆይ! እኔ በአንተ እጠበቃለሁ።" ወደ አንተ እጠጋለሁ። "ከስንፍና" የሚጠቅመኝን መዘየድ ከማልችልበት "ከመታከት" የመስራት ፍላጎትን ከማጣት፤ ሰነፍ ማለት መዘየድ የማይችል ሲሆን መታከት ማለት ደግሞ መስራት አለመፈለግ ማለት ነው። "ከፈሪነት" መስራት ለሚገባኝ ወደ ፊት ከመሄድ ከመቆጠብ፤ "ከስስታምነት" መስጠት ግዴታዬ ከሆነ ከመሰሰት "ከእርጅና" ሰውነትን የሚያደክም ከሆነ መጃጀት "ከቀብር ቅጣት" እና ለቀብር ቅጣት ከሚዳርጉ ምክንያቶች በአንተ እጠበቃለሁ። "አላህ ሆይ ለነፍሴ ፍራቻዋን ስጣት!" መልካምን ለመስራትና ወንጀልን ለመተው ግጠማት። "ነፍሴን ለማጥራት የተሻልከው አንተው ነህና ነፍሴን አጥራት" ከአንተ ውጪ ነፍሴን የሚያፀዳ አንድም የለምና ነፍሴን ከውዳቂና ርካሽ ስነምግባር አፅዳት። "አንተ ረዳቷና ተቆጣጣሪዋ ነህና።" የነፍሴን ጉዳይ የምትቆጣጠር፣ ጌታዋ፣ ባለቤቷና እርሷን የምትጣቅመው በአንተው ፀጋ ነውና። "አላህ ሆይ! እኔ ከማይጠቅም እውቀት በአንተ እጠበቃለሁ።" የኮኮብ እውቀት፣ የጥንቆላና የድግምት እውቀት አይነቱ ወይም ለመጪው አለም ከማይጠቅም እውቀት ወይም ከማይሰራበት እውቀት በአንተ እጠበቃለሁ። "አንተን ከማይፈራ ልብም በአንተ እጠበቃለሁ።" ለአንተ ከማይዋደቅ፣ ለአንተ የማይረጋ፣ አንተን በማውሳት ከማይረጋጋ ነፍስ በአንተ እጠበቃለሁ። "ከማትጠግብ ነፍስ" አላህ በሰጣትና ከለገሳት ጥሩና ሐላል ሲሳይ ከማትብቃቃ ነፍስ በአንተ እጠበቃለሁ። "ተቀባይነት ከሌላት" ተመላሽ ከሆነች "ዱዓም" በአንተ እጠበቃለሁ።"

من فوائد الحديث

  1. ሐዲሡ ውስጥ ከተጠቀሱት እነዚህ ነገሮች መጠበቅ ተወዳጅ እንደሆነ እንረዳለን።
  2. አላህን በመፍራትና እውቀትን በማሰራጨትና በእውቀት በመስራት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  3. ጠቃሚ እውቀት ማለት ነፍስን የሚያጠራ የአላህን ፍራቻ ነፍስ ውስጥ የሚፈጥርና ከነፍሱ ተነስታ ወደ ሁሉም አካላቶቹ የሚሄድን የአላህ ፍራቻ የሚያስገኝ ነው።
  4. የሚተናነስ ልብ ማለት የሚፈራ፣ የአላህ ስም ሲወሳ የምትርበተበት ከዚያም የምትረጋጋና የምትለዝብ ቀልብ ናት።
  5. ለዱንያ መጓጓትና ከስሜቶቿና ከጥፍጥናዋ አለመጥገብ መወገዙን እንረዳለን። ስለዚህም ለዱንያ ጥቅም እጅግ የምትጓጓና የምትስገበገብ ነፍስ ለሰውየው የጠላቶች ጠላት ናት። ስለዚህም ነው የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከርሷ የተጠበቁት።
  6. ሰውዬው ዱዓን ተመላሽ ከሚያደርጉና ተቀባይነትን ከሚያሳጡ ምክንያቶች ሊርቅ ይገባዋል።
  7. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥና ይህን የመሰሉ ቤት የሚመቱ ዱዓዎች ዑለሞች ለተናገሩት ማስረጃ ነው። እርሱም: ዱዓን ቤት በሚመቱ ንግግሮች ማድረግ የተወገዘው ያለ አቅሙ ቃላት ለመምረጥ ሲጥር ነው። ቃላት መረጣ መተናነስን፣ መዋደቅንና ስራን ለአላህ ማጥራትን ያስወግዳል። ከመዋደቅ፣ ፈላጊነትን ከማሳየትና በባዶ ልብ ዱዓ ከማድረግ ያዘናጋል። ነገር ግን ያለመጣጣር፣ የተሟላ አንደበተ ርቱዕ ለመሆን አይምሮን ሳያስጨንቁና የመሳሰሉትን ሳያደርጉ ወይም በሐዲሥ ውስጥ ተጠቅሶ የተሸመደደን ቤት የሚመታ ዱዓ ማለት ችግር የለውም። እንደውም የተሻለ ነው።"

عرض الترجمات

36 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية