1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ዐቂዳ (እምነት)

حديث ሙስሊም ማለት ሙስሊሞች ከምላሱና እጁ (ክፋት) ሰላም የሆኑበት ነው። ሙሃጂር (ስደተኛ) ማለት አላህ የከለከለውን የተወ ነው።

عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«المُسْلِمُ مَنْ سَلِمَ المُسْلِمُونَ مِنْ لِسَانِهِ وَيَدِهِ، وَالمُهَاجِرُ مَنْ هَجَرَ مَا نَهَى اللَّهُ عَنْهُ».

ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"ሙስሊም ማለት ሙስሊሞች ከምላሱና እጁ (ክፋት) ሰላም የሆኑበት ነው። ሙሃጂር (ስደተኛ) ማለት አላህ የከለከለውን የተወ ነው።"

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ አልቡኻሪ - 10

المعنى الإجمالي

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እስልምናው የተሟላ ሙስሊም የሚባለው ሙስሊሞች ከምላሱ ሰላም የሆኑበት ሰው እንደሆነ ተናገሩ። ስለዚህም አይሰድባቸውምም፤ አይረግማቸውምም፤ አያማቸውምም፤ በሙስሊሞች መካከል በምላስ ከሚመጡ ማናቸውም የክፋት አይነት በየትኛውም ሊጎዳቸው አይሮጥም። ከእጁም ሙስሊሞች ሰላም የሆኑበት ነው። ስለዚህም በነርሱ ላይ ወሰን አያልፍም፤ ያለ አግባብ ገንዘባቸውን አይወስድምም በሌሎች መሰል ሁኔታዎችም ሙስሊሞችን አይጎዳም። ሙሃጂር ማለት: አላህ ክልክል ያደረገውን የተወ ነው።

من فوائد الحديث

  1. የኢስላም ምሉዕነት ሌሎች ላይ ቁሳዊም ሆነ ሞራላዊ ጉዳትን ባለማድረስ ካልሆነ በቀር አይረጋገጥም።
  2. ምላስና እጅን ብቻ በማውሳት መገደቡ በነርሱ ምክንያት የሚደርስ ጉዳትና ጥፋቶች ስለሚበዙ ነው። ምክንያቱም አብዛኞቹ ክፋቶች የሚመነጩት ከሁለቱ ነውና።
  3. ወንጀልን በመተው ላይና አላህ ያዘዘውን ነገር አጥብቆ በመያዝ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  4. በላጩ ሙስሊም የሚባለው የአላህን ሐቆችና የሙስሊሞችን ሐቅ የተወጣ ነው።
  5. ወሰን አላፊነት በንግግር ወይም በተግባር ሊሆን ይችላል።
  6. የተሟላ ሂጅራ የሚባለው አላህ ክልክል ያደረገውን በመተው ነው።

عرض الترجمات

57 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
KY Кыргызча القيرقيزية
NE नेपाली النيبالية
YO Yorùbá اليوروبا
LT Lietuvių الليتوانية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
SO Soomaali الصومالية
TG тоҷикӣ الطاجيكية
RW Kinyarwanda الكينياروندا
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
CS Čeština التشيكية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
IT Italiano الإيطالية
OM Oromoo الأورومو
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
AZ Azərbaycan الأذربيجانية
UZ O‘zbek الأوزبكية
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية
KMR Kurmancî الكرمنجية