1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

حديث ለአንድ አማኝ ከዱንያ ችግሮቹ መካከል አንዱን ችግሩን ያቀለለለት ሰው አላህም ከትንሳኤ ቀን ችግሮቹ መካከል አንድን ችግሩን ያቀልለታል።

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَنْ نَفَّسَ عَنْ مُؤْمِنٍ كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ الدُّنْيَا نَفَّسَ اللهُ عَنْهُ كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ يَوْمِ الْقِيَامَةِ، وَمَنْ يَسَّرَ عَلَى مُعْسِرٍ يَسَّرَ اللهُ عَلَيْهِ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ، وَمَنْ سَتَرَ مُسْلِمًا سَتَرَهُ اللهُ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ، وَاللهُ فِي عَوْنِ الْعَبْدِ مَا كَانَ الْعَبْدُ فِي عَوْنِ أَخِيهِ، وَمَنْ سَلَكَ طَرِيقًا يَلْتَمِسُ فِيهِ عِلْمًا سَهَّلَ اللهُ لَهُ بِهِ طَرِيقًا إِلَى الْجَنَّةِ، وَمَا اجْتَمَعَ قَوْمٌ فِي بَيْتٍ مِنْ بُيُوتِ اللهِ يَتْلُونَ كِتَابَ اللهِ وَيَتَدَارَسُونَهُ بَيْنَهُمْ إِلَّا نَزَلَتْ عَلَيْهِمِ السَّكِينَةُ، وَغَشِيَتْهُمُ الرَّحْمَةُ، وَحَفَّتْهُمُ الْمَلَائِكَةُ، وَذَكَرَهُمُ اللهُ فِيمَنْ عِنْدَهُ، وَمَنْ بَطَّأَ بِهِ عَمَلُهُ لَمْ يُسْرِعْ بِهِ نَسَبُهُ».

ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
"ለአንድ አማኝ ከዱንያ ችግሮቹ መካከል አንዱን ችግሩን ያቀለለለት ሰው አላህም ከትንሳኤ ቀን ችግሮቹ መካከል አንድን ችግሩን ያቀልለታል። የተጨነቀ ሰውን ከጭንቁ ለገላገለ ሰው አላህም በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ጭንቀቱን ያቀልለታል። የሙስሊምን ነውር ለሸሸገ ሰው አላህም በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ነውሩን ይሸሽግለታል። የአላህ ባሪያ ወንድሙን በማገዝ ላይ እስከሆነ ድረስ አላህም ባሪያውን በማገዝ ላይ ነው። እውቀትን ለመፈለግ መንገድ የተጓዘ ሰው አላህም በርሱ ምክንያት የጀነትን መንገድ ያገራለታል። ሰዎች የአላህን መጽሐፍ ሊያነቡና በመካከላቸው ሊማማሩት ከአላህ ቤቶች መካከል አንድ ቤት ውስጥ እስከተሰባሰቡ ድረስ አላህም በነርሱ ላይ ሰኪናውን (እርጋታውን) ያወርድላቸዋል፤ በእዝነቱ ይሸፍናቸዋል፤ መላእክቶችም ያካብቧቸውና አላህም እርሱ ዘንድ ካሉት ጋር ያወሳቸዋል። ስራው ወደኋላ ያስቀረውን ሰው ዘሩ አያስቀድመውም።"»

ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ ሙስሊም - 2699

المعنى الإجمالي

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ ሙስሊም አላህ ዘንድ የሚመነዳው ከሙስሊሞች ጋር ከሚሰራው የስራ አይነት አንፃር እንደሆነ ገለፁ። ከአንድ አማኝ ላይ ከዱንያ ችግሮች መካከል አንድን ችግርና መከራ ያቀለለ፣ የገላገለ፣ ያስወገደና ያነሳ ሰው አላህም ከትንሳኤ ቀን ችግሮች መካከል አንድን ችግሩን በማቅለል ይመነዳዋል። ለተቸገረ ያቀለለ፣ ያገራ፣ ችግሩንም ያስወገደ አላህም ለርሱ በዱንያም ሆነ በመጪው ዓለም ጉዳዩን ያቀልለታል። የሙስሊምን ነውር - ለምሳሌ ግልፅ መውጣት የማይገባውን ስህተትና ጥፋት እርሱ ላይ አይቶ - የሸሸገለት ሰው አላህ በዱንያም ሆነ በመጪው ዓለም ነውሩን ይሸሽግለታል። አንድ ሰው ወንድሙን ዲናዊም ይሁን ዱንያዊ ጥቅሞቹ ላይ እስካገዘው ድረስ አላህም ባሪያውን በማገዝ ላይ ይሆናል። ማገዝ በዱዓ፣ በአካል፣ በገንዘብና ከዚህም ውጪ ባሉ ነገሮች ይፈፀማል። የአላህን ፊት ፈልጎበት ሸሪዓዊ ዕውቀትን ለማግኘት የተጓዘን ሰው ወደ ጀነት የሚያደርሰውን መንገድ አላህ ያገራለታል። ሰዎች የአላህን መጽሐፍ ሊያነቡና በመካከላቸው ሊማማሩት ዘንድ ከአላህ ቤቶች መካከል አንድ ቤት ውስጥ ከተሰባሰቡ በነርሱ ላይ እርጋታና ስክነት ይሰፍናል፤ የአላህ እዝነትም ይሸፍናቸዋል፤ መላዕክቶች ያካብቧቸዋል፤ አላህ ዘንድ ቅርብ ከሆኑት ጋር ያሞግሳቸዋል (ያወድሳቸዋል)። አላህ ባሪያውን በላይኛው አለም ማውሳቱ ብቻ ከክብር በቂ ነው። ስራው ጎዶሎ የሆነ ሰው የተሟላ ስራ የሰሩ ሰዎች ደረጃ ላይ አይደርስም። ስለዚህ በዘር ልቅናና በወላጆች ደረጃ ተማምኖ መልካም ስራን ማጓደል አይገባም።

من فوائد الحديث

  1. ኢብኑ ደቂቅ አልዒዲ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ትልቅና የተለያዩ ዕውቀቶችን፣ መርሆችንና ስነስርዓቶችን የጠቀለለ ሐዲሥ ነው። ይህ ሐዲሥ ሙስሊሞችን ጉዳያቸውን በመፈፀምና በተቻለው መጠን በዕውቀት ወይም በገንዘብ ወይም በእገዛ ወይም ጠቃሚን ነገር በመጠቆም ወይም በምክር ወይም ከዚህ ውጪ ባሉ ነገሮች ሁሉ መጥቀም እንደሚገባ ያስረዳናል።"
  2. ለተቸገረ ሰው ችግሩን በማቅለል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  3. ሙስሊምን በማገዝ ላይ መነሳሳቱንና ወንድሙን ባገዘበት ልክም አላህም አጋዡን ሰው እንደሚያግዘው እንረዳለን።
  4. ሙስሊምን ከመሸሸግ መካከል ነውሩን አለመከታተል አንዱ ነው። ከሰለፎች ከአንዱ እንዲህ ማለቱ ተዘግቧል "ነውር የሌለባቸው ሰዎች አጋጥመውኛል። የሌሎችን ነውር ያወሩ እለት ግን ሰዎችም የነርሱን ነውር አወሩባቸው። ነውር የነበረባቸው ሰዎችም አጋጥመውኛል። የሰዎችን ነውር ከማውራት የተቆጠቡ እለት ነውራቸውም ተረሳች።"
  5. የሰዎችን ነውር መሸሸግ ማለት እነርሱን አለመምከርና እንዲለወጡ አለማድረግ ማለት አይደለም። ይልቁንም ከመሸሸግም ጋር እንለውጠዋለን። ይህም ማበላሸትና ጥመት ላይ በመዘውተሩ መገለጫው እስኪሆን የደረሰውን አይመለከትም። በዚህ ባህሪ የታወቀ ከሆነ ግን የርሱን ነውር መሸሸግ አይወደድም። ይልቁንም የባሰ መዘዝ እንዳይመጣ ስጋት እስከሌለ ድረስ በርሱ ጉዳይ እርምጃ መውሰድ ወደሚችል ሰው እንወስደዋለን። ይህም ለርሱ ነውሩን መሸሸግ በማበላሸቱ ላይ እንዲታለል፤ ሰዎችን ወደ ማወክ እንዲያመራ ስለሚያደርግና ከርሱ ውጪ ያሉ የክፋትና የአመፅ ባለቤቶችንም ስለሚያደፋፍር ነው።
  6. ዕውቀትን በመፈለግ፣ ቁርአንን በማንበብና በመማማር ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  7. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: ይህ ሐዲሥ መስጂድ ውስጥ ቁርአንን ለማንበብ መሰብሰብ ያለውን ትሩፋት ይጠቁማል። ... መድረሳ ውስጥ፣ ዛውያና የመሳሰሉት ውስጥ መሰባሰብም ኢንሻአላህ (በአላህ ፈቃድ) ይህን ደረጃ እንደሚያስገኝ ተስፋ እናደርጋለን።
  8. አላህ ምንዳን ያስቀመጠው በተግባር ነው እንጂ በዘር አይደለም።

عرض الترجمات

60 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
FR Français الفرنسية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
JA 日本語 اليابانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
KY Кыргызча القيرقيزية
NE नेपाली النيبالية
LT Lietuvių الليتوانية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
TG тоҷикӣ الطاجيكية
RW Kinyarwanda الكينياروندا
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
CS Čeština التشيكية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
OM Oromoo الأورومو
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
AZ Azərbaycan الأذربيجانية
UZ O‘zbek الأوزبكية
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
BM Bambara البامبارية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية
DA Dansk الدنماركية
RN Kirundi الكيروندي
KMR Kurmancî الكرمنجية
MS Bahasa Melayu الملايو