1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

حديث ጀነት ውስጥ ረያን የሚባል በር አለ። የትንሳኤ ቀን ጾመኞች በርሱ በኩል ይገባሉ። በርሱ በኩልም ከነርሱ ውጪ አንድም ሰው አይገባም።

عَنْ ‌سَهْلٍ رَضِيَ اللهُ عَنْهُ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِنَّ فِي الْجَنَّةِ بَابًا يُقَالُ لَهُ الرَّيَّانُ، يَدْخُلُ مِنْهُ الصَّائِمُونَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ، لَا يَدْخُلُ مِنْهُ أَحَدٌ غَيْرُهُمْ، يُقَالُ: أَيْنَ الصَّائِمُونَ، فَيَقُومُونَ لَا يَدْخُلُ مِنْهُ أَحَدٌ غَيْرُهُمْ، فَإِذَا دَخَلُوا أُغْلِقَ، فَلَمْ يَدْخُلْ مِنْهُ أَحَدٌ».

ከሰህል ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
«ጀነት ውስጥ ረያን የሚባል በር አለ። የትንሳኤ ቀን ጾመኞች በርሱ በኩል ይገባሉ። በርሱ በኩልም ከነርሱ ውጪ አንድም ሰው አይገባም። "ጾመኞች የት አሉ?" ይባላል። እነርሱም ይቆማሉ። በርሱ በኩልም ከነርሱ ውጪ አንድም ሰው አይገባም። እነርሱ የገቡ ጊዜ ይዘጋል። በርሱ በኩል ማንም አይገባም።»

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1896

المعنى الإجمالي

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከጀነት በሮች መካከል "የረያን በር" ተብሎ የሚጠራ በር እንዳለና የትንሳኤ ቀን በርሱ በኩል ጾመኞች እንደሚገቡበት ተናገሩ። ከነርሱ ውጪም በርሱ በኩል አንድም ሰው እንደማይገባበት፤ "ጾመኞች የት አሉ?" ተብሎም እንደሚለፈፍ፤ ጾመኞችም ተነስተው እንደሚገቡ፤ በርሱ በኩል ከነርሱ ውጪ ማንም እንደማይገባበት፤ የመጨረሻቸው ሰው ከገባ በኃላ እንደሚዘጋና ከዛ በኋላም በርሱ በኩል ማንም እንደማይገባበት ተናገሩ።

من فوائد الحديث

  1. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ የጾምን ደረጃና የጾመኞችን ክብር ያሳየናል።"
  2. አላህ ለጾመኞች ከጀነት ስምንት በሮች መካከል አንድ በር ለብቻቸው አዘጋጅቷል። እነርሱ የገቡ ጊዜም ይዘጋል።
  3. ጀነት በሮች እንዳላት መገለፁን ተረድተናል።
  4. ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "(ጾመኞች የት አሉ?) የሚለው ንግግር ጾም የሚያበዙ የት አሉ? ለማለት ነው። ፍትሃዊ ግፈኛ እንደሚባለው ማለት ነው። ይህ የሚባለውም ልምዱ አድርጎ ለያዘው ሰው ነው እንጂ አንዴ ለፈፀመው ሰው አይደለም።"
  5. (ረያን) ማለት የሚያረካ ማለት ነው። ምክንያቱም ጾመኞች በተለይ በበጋ ቀናት ቀኑ ሀሩራማና ረጅም በሆነበት ጊዜ ሲጾሙ ይጠማሉ። ለነርሱ ብቻ የተለየን ይህ በር "የረያን በር" በሚል በዚህ ስያሜ በመሰየም ይመነዳሉ። ረያን ማለት እጅግ መርካት የጥም ተቃራኒ ማለት ሲሆን በዚህም የተሰየመው ጾመኞች በጥማቸውና በረሃባቸው የሚመነዱበት ስለሆነ ነውም ተብሏል።

عرض الترجمات

40 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية