1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

حديث የአደም ልጅ ሁለት በገንዘብ የሞላ ሸለቆ ቢኖረው ኖሮ ሶስተኛ ሸለቆ ይመኛል።

عَنْ أَنَسٍ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«لَوْ كَانَ لِابْنِ آدَمَ وَادِيَانِ مِنْ مَالٍ لَابْتَغَى وَادِيًا ثَالِثًا، وَلَا يَمْلَأُ جَوْفَ ابْنِ آدَمَ إِلَّا التُّرَابُ، وَيَتُوبُ اللهُ عَلَى مَنْ تَابَ».

አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዳስተላለፉት እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦
"የአደም ልጅ ሁለት በገንዘብ የሞላ ሸለቆ ቢኖረው ኖሮ ሶስተኛ ሸለቆ ይመኛል። የአደምን ልጅ ሆድ ከአፈር በቀር የሚሞላው የለም። ወደ አላህ ተፀፅቶ በተመለሰ ሰው ላይም አላህ ተውበቱን ይቀበለዋል።"»

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ ሙስሊም - 1048

المعنى الإجمالي

ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - የአደም ልጅ በወርቅ የሞላ ሸለቆ ቢኖረው ኖሮ በተፈጥሮው ካለው ስግብግብነት አንፃር ሌሎች ሁለት ሸለቆዎችን ይመኝ ነበር። የአደም ልጅ ሙቶ ከርሱ በቀብሩ አፈር ካልሞላ በቀር ለዱንያ ስግብግብ ከመሆን አይወገድም።

من فوائد الحديث

  1. የሰው ልጅ ገንዘብንና ሌሎችንም ዱንያዊ መጣቀሚያ በማግበስበስ ላይ ያለውን ከፍተኛ ጉጉት ያስረዳናል።
  2. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ከዚህ ሐዲሥ ለዱንያ መጓጓት፣ ዱንያን ማብዛትና እርሷን መከጀል የተወገዘ መሆኑን እንረዳለን።"
  3. አላህ ከተወገዘ ባህሪ ተፀፅቶ የሚመለስን ሰው ተውበት ይቀበላል።
  4. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ የብዙሃኑን የአደም ልጆች የዱንያ ጉጉት ነው የገለፀው ይህንንም (ተፀፅቶ ተውበት ባደረገ ሰው ላይ አላህም ተውበቱን ይቀበለዋል።) የሚለው የነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና -ንግግር ያጠናክረዋል።"

عرض الترجمات

36 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية