1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

حديث የአላህ ቃል የበላይ እንድትሆን አስቦ የተዋጋ ሰው በአላህ መንገድ ተጋደለ የሚባለው እርሱ ነው።" አሉ።

عَنْ أَبِي مُوسَى رضي الله عنه قَالَ:
سُئِلَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَنِ الرَّجُلِ يُقَاتِلُ شَجَاعَةً، وَيُقَاتِلُ حَمِيَّةً، وَيُقَاتِلُ رِيَاءً، أَيُّ ذَلِكَ فِي سَبِيلِ اللهِ؟ فَقَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «مَنْ قَاتَلَ لِتَكُونَ كَلِمَةُ اللهِ هِيَ الْعُلْيَا، فَهُوَ فِي سَبِيلِ اللهِ».

ከአቡ ሙሳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለጀግንነት ስለሚጋደል፣ ለወገንተኝነት ስለሚጋደልና ለይዩልኝ ስለሚጋደል ሰው ተነስቶ ‹በአላህ መንገድ የተጋደለው የትኛው ነው?› ተብለው ተጠየቁ። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "የአላህ ቃል የበላይ እንድትሆን አስቦ የተዋጋ ሰው በአላህ መንገድ ተጋደለ የሚባለው እርሱ ነው።" አሉ።

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ ሙስሊም - 1904

المعنى الإجمالي

ነቢዩ ( የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተዋጊዎች አላማ ስለመለያየት ተጠየቁ። ለጀግንነት ወይም ለወገንተኝነት ወይም ደረጃው ሰው ዘንድ እንዲታይለት ወይም ከዚህ ውጪ ላለ አላማም ከተጋደለ ሰው መካከል በአላህ መንገድ ተጋደለ የሚባለው ማንኛው ነው? ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአላህ መንገድ የሚጋደል የሚባለው ሰው የአላህ ቃል የበላይ እንድትሆን የተጋደለ ሰው መሆኑን ተናገሩ።

من فوائد الحديث

  1. የሥራዎች መስተካከያና መበላሻው መሰረቱ ኒያና ሥራን ለአላህ ማጥራት ነው።
  2. የጂሃዱ መሰረታዊ አላማ የአላህን ቃል የበላይ ማድረግ ከሆነና ከዚህ ጋር አክሎም ሌላ አላማ ቢጨምርበት (ምርኮ ማግኘትን ይመስል) የኒያውን መሰረት አይጎዳውም።
  3. ጠላቶችን ከሀገር እና ከዳር ድንበር መከላከል በአላህ መንገድ መዋጋት ውስጥ ይመደባል።
  4. በሙጃሂዶች ዙሪያ የተጠቀሱ ትሩፋቶች የአላህን ቃል የበላይ እንዲሆን የተዋጉ ሰዎችን ብቻ የሚመለከት ነው።

عرض الترجمات

58 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
FR Français الفرنسية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
KY Кыргызча القيرقيزية
NE नेपाली النيبالية
YO Yorùbá اليوروبا
LT Lietuvių الليتوانية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
SO Soomaali الصومالية
TG тоҷикӣ الطاجيكية
RW Kinyarwanda الكينياروندا
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
CS Čeština التشيكية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
OM Oromoo الأورومو
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
AZ Azərbaycan الأذربيجانية
UZ O‘zbek الأوزبكية
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية
KMR Kurmancî الكرمنجية