1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ዐቂዳ (እምነት)

حديث ‹ከፈለግሽ ታግሰሽ ላንቺ ጀነት አለሽ። ከፈለግሽ ደሞ ጤናን እንዲለግስሽ አላህን እለምንልሻለሁኝ።›

عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ رضيَ اللهُ عنهما:
أنَّهُ قَالَ لعَطَاءِ بْنِ أَبِي رَبَاحٍ: أَلَا أُرِيكَ امْرَأَةً مِنْ أَهْلِ الْجَنَّةِ؟ قُلْتُ: بَلَى، قَالَ: هَذِهِ الْمَرْأَةُ السَّوْدَاءُ، أَتَتِ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، قَالَتْ: إِنِّي أُصْرَعُ وَإِنِّي أَتَكَشَّفُ، فَادْعُ اللهَ لِي، قَالَ: «إِنْ شِئْتِ صَبَرْتِ وَلَكِ الْجَنَّةُ، وَإِنْ شِئْتِ دَعَوْتُ اللهَ أَنْ يُعَافِيَكِ» قَالَتْ: أَصْبِرُ، قَالَتْ: فَإِنِّي أَتَكَشَّفُ فَادْعُ اللهَ أَنْ لَا أَتَكَشَّفَ، فَدَعَا لَهَا.

ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:
ኢብኑ ዓባስ ለዐጧእ ቢን አቢ ረባሕ እንዲህ አሉ:«ከጀነት ሰዎች መካከል የሆነች ሴት አላሳይህምን?" እኔም "እንዴታ!" አልኩኝ። እርሳቸውም እንዲህ አሉኝ: "ይህቺ ጥቁር ሴት ናት። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣችና እንዲህ አለች: ‹እኔ የሚጥል በሽታ አለብኝና እገላለጣለሁ። እንዲፈውሰኝ አላህን ለምኑልኝ።› እርሳቸውም: ‹ከፈለግሽ ታግሰሽ ላንቺ ጀነት አለሽ። ከፈለግሽ ደሞ ጤናን እንዲለግስሽ አላህን እለምንልሻለሁኝ።› አሏት። እርሷም ‹እታገሳለሁ።› ብላ እንዲህም አለች: ‹እኔ እገላለጣለሁኝ። እንዳልገላለጥ አላህን ለምኑልኝ።› እርሳቸውም ዱዓ አደረጉላት።"»

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ ሙስሊም - 2576

المعنى الإجمالي

ኢብኑ ዐባስ (አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና) ለዐጧእ ቢን አቢረባሕ እንዲህ አሉ: "የጀነት ነዋሪ የሆነችን ሴት አላሳይህምን?" ዐጧእም "እንዴታ!" አለ። ኢብኑ ዐባስም እንዲህ አሉ: "ይህቺ ሐበሻዊት ጥቁር ሴት ናት። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣችና እንዲህ አለች: "የሚጥል በሽታ ስላለብኝ ይጥለኝና እገላለጣለሁኝ። ታዲያ እኔ ሳላውቀው ከሰውነቴ የተወሰነው ክፍል ይገለጣል። አላህ ጤናን እንዲለግሰኝ ለምኑልኝ።" እርሳቸውም እንዲህ አሏት: "ከፈለግሽ ታግሰሽ ላንቺ ጀነት አለልሽ። ከፈለግሽ ደግሞ አላህ ጤናን እንዲሰጥሽ እለምንልሻለሁኝ።" እርሷም እንዲህ አለች: "እንዲህ ከሆነ እታገሳለሁኝ። አክላም "ስወድቅ እንዳልገላለጥ ግን አላህን ይለምኑልኝ።" አለች። እርሳቸውም አላህን ለመኑላት።

من فوائد الحديث

  1. በዱንያ በሚያጋጥሙ መከራዎች ላይ መታገስ ጀነትን ያስወርሳል።
  2. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ የሚጥል በሽታ የተሟላን ምንዳ እንደሚያስመነዳ ይጠቁማል።"
  3. ሴት ሶሓቦች (አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና) የነበራቸውን ሀፍረትና ጥብቅነት እንዲሁም ለመሸፈን የነበራቸውን ጥረት እንረዳለን። ይህቺ ሴት አብዝታ ትፈራ የነበረው ጉዳይ ከሰውነቷ አንዳች አካል እንዳይገለጥባት ነበር።
  4. ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ነፍሱ አቅም እንዳላት የተረዳና በጠንካራው ትእዛዝ ለመዘውተር ያልደከመ ሰው የተግራራውን ትእዛዝ ከመተግበር ይልቅ ጠንካራውን ትእዛዝ መተግበሩ ይበልጥለታል።"
  5. ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ በሽታዎችን ሁሉ በዱዓ፣ ወደ አላህ በመጠጋት ማከም በመድሓኒቶች ከመፈወስ የበለጠ ፈዋሽና ጠቃሚ እንደሆነ፣ የዱዓ ተፅእኖና የሚፈጥረው አካላዊ መነቃቃትም መድሃኒቶች ከሚፈጥሩት ተፅእኖ እጅግ የላቀ እንደሆነ እንረዳለን። ነገር ግን ይህ ስኬታማ የሚሆነው ሁለት ነገሮች ሲሟሉ ነው: የመጀመሪያው የሚፈለገው ከታማሚው ሲሆን እርሱም: በትክክል እድናለሁኝ የሚል ሃሳብ መሰነቅ ነው። ሁለተኛው: ከሚያክመው ሰው የሚፈለግ ሲሆን: ወደ አላህ የዞረበት ጥንካሬና ቀልቡ አላህን በመፍራትና በአላህ በመመካት የበረታ መሆኑ ነው።" አላህ የበለጠ አዋቂ ነው።
  6. ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ህክምናን መተውም እንደሚፈቀድ ይጠቁማል።"

عرض الترجمات

36 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية