1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

حديث ወደ ሰማይ እንዳርግ በተደረግኩበት ወቅት የነሃስ ጥፍር ባላቸውና በነዛም ጥፍሮች ፊቶቻቸውንና ደረቶቻቸውን በሚቧጭሩ ሰዎች በኩል አለፍኩ።

عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«لَمَّا عُرِجَ بِي مَرَرْتُ بِقَوْمٍ لَهُمْ أَظْفَارٌ مِنْ نُحَاسٍ يَخْمُشُونَ بها وُجُوهَهُمْ وَصُدُورَهُمْ، فَقُلْتُ: مَنْ هَؤُلَاءِ يَا جِبْرِيلُ، قَالَ: هَؤُلَاءِ الَّذِينَ يَأْكُلُونَ لُحُومَ النَّاسِ، وَيَقَعُونَ فِي أَعْرَاضِهِمْ».

አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዳስተላለፉት እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦
«ወደ ሰማይ እንዳርግ በተደረግኩበት ወቅት የነሃስ ጥፍር ባላቸውና በነዛም ጥፍሮች ፊቶቻቸውንና ደረቶቻቸውን በሚቧጭሩ ሰዎች በኩል አለፍኩ። እኔም "ጂብሪል ሆይ! እነዚህ እነማን ናቸው?" ብዬ ጠየቅኩት። እርሱም "እነዚህ የሰዎችን ስጋ የሚበሉና የሰዎችን ክብር የሚያጎድፉ ናቸው።" በማለት መለሰልኝ።»

ሐሰን ነው። አቡዳውድ ዘግበውታል። ሱነን አቡዳውድ - 4878

المعنى الإجمالي

ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - በኢስራእና ሚዕራጅ ምሽት ወደ ሰማይ በወጡበት ወቅት የነሃስ ጥፍሮች ባሏቸውና ፊቶቻቸውንና ደረቶቻቸውንም በሚቧጭሩና በሚቦጭቁ ሰዎች በኩል እንዳለፉ ተናገሩ። ነቢዩም - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጂብሪልን ዐለይሂ ሰላም እነዚህ ሰዎች በዚህ ቅጣት እንዲመነዱ ያደረጋቸው ምንድነው? ብለው ጠየቁት። ጂብሪልም ዐለይሂ ሰላም እነዚህ ሰዎችን የሚያሙና ያለአግባብ ስለሰዎች ክብር የሚናገሩ ናቸው። ብሎ መለሰላቸው።

من فوائد الحديث

  1. ሃሜትን በማስመልከት ከባድ ማስጠንቀቂያ መምጣቱንና የሚያማ ሰው የሰውን ስጋ ከመብላት ጋር እንደተመሳሰለ እንረዳለን።
  2. በሃሜትና በመሳሰሉት የሰዎችን ክብር መንካት ከትላልቅ ወንጀሎች እንደሆነ እንረዳለን።
  3. ጢቢይ "የሚቧጭሩ" በሚለው የሐዲሡ ቃል ዙሪያ እንዲህ ብለዋል: "ፊትንና ደረትን መቧጨር የሙሾ አውራጅ ሴቶች ባህሪ ከመሆኑ አንፃር የሙስሊሞችን ክብር ለሚያጎድፉ ሰዎችም መቀጫቸው ያንኑ ባህሪ መላበስ አደረገው። ይህም ሁለቱም ባህሪያት የወንዶች ሳይሆኑ የሴቶች ለዛውም በአስቀያሚ ሁኔታና በመጥፎ ገፅታ ላይ ሲሆኑ የሚላበሱት ባህሪ እንደሆነ የሚገልፅ ነው።"
  4. በሩቅ እውቀትና አላህና መልክተኛው - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - በተናገሩት ባጠቃላይ ማመን ግዴታ እንደሆነ እንረዳለን።

عرض الترجمات

37 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية