1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ዐቂዳ (እምነት)

حديث የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመከራ ወቅት ከምትጮህ፣ ከምትላጭና ልብሷን ከምትቀዳድድ ራሳቸውን አጥርተዋል።

عَن أَبِي بُرْدَةَ بْنِ أَبِي مُوسَى رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ:
وَجِعَ أَبُو مُوسَى وَجَعًا شَدِيدًا، فَغُشِيَ عَلَيْهِ وَرَأْسُهُ فِي حَجْرِ امْرَأَةٍ مِنْ أَهْلِهِ، فَلَمْ يَسْتَطِعْ أَنْ يَرُدَّ عَلَيْهَا شَيْئًا، فَلَمَّا أَفَاقَ، قَالَ: أَنَا بَرِيءٌ مِمَّنْ بَرِئَ مِنْهُ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، إِنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ بَرِئَ مِنَ الصَّالِقَةِ وَالحَالِقَةِ وَالشَّاقَّةِ.

ከአቢ ቡርዳህ ቢን አቢ ሙሳ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ:
«አቡ ሙሳ ከባድ ህመምን ታመመና ራሱን ሳተ። ጭንቅላቱ ሚስቱ ታፋ ላይ ነበር። (ስታለቅስና ስትገጥም) በርሷ ላይ አንዳችም መልስ መስጠት አልቻለም ነበር። የነቃ ጊዜ "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ራሳቸውን ካጠሩት ሰው እኔም የጠራሁ ነኝ። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመከራ ወቅት ከምትጮህ፣ ከምትላጭና ልብሷን ከምትቀዳድድ ራሳቸውን አጥርተዋል።"»

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1296

المعنى الإجمالي

አቡቡርዳህ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - አባቱ አቡ ሙሳ አልአሽዐሪይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከባድ በሽታ እንደታመመና ራሱን እንደሳተ ተናገረ። ጭንቅላቱም ባለቤቱ ታፋ ላይ ነበር። እርሷም እየጮኸች ሙሾ አወረደች። ራሱን ስቶ ስለነበረ አንዳችም ሊመልስላት አልቻለም ነበር። የነቃም ጊዜ እንዲህ አለ: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ራሳቸውን ካጠሩት ሁሉ እኔም አጥርቻለሁ። ነቢዩ: (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከነዚህ ራሳቸውን አጥርተዋል: ከ "ሷሊቃህ": በመከራ ወቅት ድምጿን ከፍ ከምታደርግ፤ ከ "ሓሊቃህ": በመከራ ወቅት ፀጉሯን ከምትላጭ፤ ከ "ሻቃህ": በመከራ ወቅት ልብሷን ከምትቀዳድ የጠራሁ ነኝ ብለዋል። እነዚህ ነገሮች የድንቁርናው ዘመን መገለጫ ስለሆኑ ነው። ይልቁንም በመከራ ወቅት ትእግስት በማድረግና ምንዳውን አላህ ዘንድ በማሰብ አዘዙ።

من فوائد الحديث

  1. መከራ በሚከሰት ወቅት ልብስን ከመቅደድ፣ ፀጉርን ከመላጨትና ከመጮህ መከልከሉንና ይህም ከትላልቅ ወንጀሎች መሆኑን እንረዳለን።
  2. ሙሾ ማውረድና መጮህ የሌለበት ማልቀስና ማዘን ክልክል አይደለም። ይህም በአላህ ውሳኔ ላይ ከመታገስ ጋር አይጋጭም። እንደውም ይህ የሚያሳየው ሃዘኔታን ነው።
  3. አሳማሚ የሆኑ የአላህ ውሳኔዎችን በንግግርም ይሁን በድርጊት ማማረር ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
  4. መከራ በሚከሰት ወቅት ትእግስት ማድረግ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።

عرض الترجمات

46 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
NE नेपाली النيبالية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية