1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

حديث ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ገላቸውን ከአንድ ቁና ውሃ እስከ አምስት እፍኝ ድረስ ባለ ውሃ ያጥቡ ወይም ይታጠቡ ነበር። በአንድ እፍኝ ደግሞ ዉዱእ ያደርጉ ነበር።

عَنْ أَنَسٍ رضي الله عنه قَالَ:
كَانَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَغْسِلُ، أَوْ كَانَ يَغْتَسِلُ، بِالصَّاعِ إِلَى خَمْسَةِ أَمْدَادٍ، وَيَتَوَضَّأُ بِالْمُدِّ.

ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦
"ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ገላቸውን ከአንድ ቁና ውሃ እስከ አምስት እፍኝ ድረስ ባለ ውሃ ያጥቡ ወይም ይታጠቡ ነበር። በአንድ እፍኝ ደግሞ ዉዱእ ያደርጉ ነበር።"

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ አልቡኻሪ - 201

المعنى الإجمالي

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከአንድ ቁና እስከ አምስት እፍኝ በሚደርስ ውሃ ከጀናባ ይታጠቡ ነበር። በአንድ እፍኝ ደግሞ ዉዱእ ያደርጉ ነበር። ቁና ማለት አራት እፍኝ ውሃ ማለት ሲሆን እፍኝ ማለት ደግሞ መካከለኛ ተፈጥሮ ያለው ሰው በሁለቱ መዳፎቹ ሙሉ የሚያክል ነው።

من فوائد الحديث

  1. የዉዱእና የትጥበት ውሃ ላይ ቆጣቢ መሆንና ውሃው ትንሽ ቢሆን እንኳ አለማባከን እንደሚገባ እንረዳለን።
  2. የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መመሪያ ስለሆነ እንደአስፈላጊነቱ የዉዱእና የትጥበት ውሃን ማሳነስ እንደሚወደድ እንረዳለን።
  3. ከዉዱእና ትጥበት የሚፈለገው ሳይሰስቱና ሳያባክኑ አዳቡና ሱናውን ከመጠበቅ ጋር አሟልቶ መፈፀም ነው። ወቅቱን፣ የውሃውን ብዛትና ማነስ የመሳሰሉትን ግምት ውስጥ አስገብቶ ማድረግ ነው።
  4. ጀናባ የሚለው ስም የዘር ፈሳሽ ያፈሰሰ ወይም ግንኙነት የፈፀመ ሁሉ የሚገለፅበት ስም ነው። በዚህም የተሰየመው እስኪፀዳ ድረስ ግለሰቡ ከሶላትና ከአምልኮ ስለሚርቅ ነው።
  5. ቁና: የታወቀ መለኪያ ነው። የተፈለገውም ነቢያዊው ቁና ነው። የሚመዝነውም ጥሩ በሆነ የስንዴ ዘር (480) ግራም የሚመዝን ነው። በሊትር ደግሞ (3 ሊትር) የሚይዝ ነው።
  6. እፍኝ: አንዱ ሸሪዓዊ መስፈሪያ ነው። እርሱም መካከለኛ የሆነ ሰው መዳፍ እጁን ዘርግቶ በሁለት እጁ የሚዘግነውን ያህል ማለት ነው። አንድ እፍኝ በፉቀሃዎች ባጠቃላይ ስምምነት የአንድ ቁና ሩብ ነው። መጠኑም (750) ሚ·ሊ ይመዝናል።

عرض الترجمات

52 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
KY Кыргызча القيرقيزية
NE नेपाली النيبالية
LT Lietuvių الليتوانية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
TG тоҷикӣ الطاجيكية
RW Kinyarwanda الكينياروندا
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
CS Čeština التشيكية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
OM Oromoo الأورومو
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
AZ Azərbaycan الأذربيجانية
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية