1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

حديث ሰዎች ሶላታቸው ውስጥ ሆነው ዓይኖቻቸውን ወደ ሰማይ ከፍ የሚያደርጉት ምን ሆነው ነው!?" በዚህ ዙሪያም አጠንክረው አስጠነቀቁ። እንዲህም አሉ "ከዚህ ተግባራቸው ይከልከሉ ወይም አይናቸው ትነጠቃለች።

عَن أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَا بَالُ أَقْوَامٍ يَرْفَعُونَ أَبْصَارَهُمْ إِلَى السَّمَاءِ فِي صَلاَتِهِمْ»، فَاشْتَدَّ قَوْلُهُ فِي ذَلِكَ، حَتَّى قَالَ: «لَيَنْتَهُنَّ عَنْ ذَلِكَ أَوْ لَتُخْطَفَنَّ أَبْصَارُهُمْ».

ከአነስ ቢን ማሊክ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
"ሰዎች ሶላታቸው ውስጥ ሆነው ዓይኖቻቸውን ወደ ሰማይ ከፍ የሚያደርጉት ምን ሆነው ነው!?" በዚህ ዙሪያም አጠንክረው አስጠነቀቁ። እንዲህም አሉ "ከዚህ ተግባራቸው ይከልከሉ ወይም አይናቸው ትነጠቃለች።"»

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል። ሶሒሕ አልቡኻሪ - 750

المعنى الإجمالي

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሶላት ውስጥ ሆነው ዱዓ ሲያደርጉም ይሁን ሌላ ድርጊት ሲያደርጉ አይኖቻቸውን ወደ ሰማይ ከፍ የሚያደርጉ ሰዎችን አስጠነቀቁ። ቀጥለውም ይህንን በሚፈፅሙ ሰዎች ላይ ማስጠንቀቂያቸውንና ዛቻቸውን አበረቱ። በማያውቁት መልኩ የማየትን ፀጋ በሚያጡበት ሁኔታ አይኖቻቸውን የመነጠቅና በፍጥነት የመጥፋት አደጋ እንደሚፈራለትም አሳሰቡ።

من فوائد الحديث

  1. የነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ጥሪ ያማረ መሆኑንና እውነትን ባመረ መልኩ እንደሚያብራሩ ተረድተናል። የነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አላማ እውነቱን መግለፅ ስለሆነና ያንንም ስላሳኩ ይህንን የተቃረነውን ግለሰብ አላጋለጡትም። ይህን በማድረጋቸውም የተቃረነውን ግለሰብ ነውሩ ተሸሽጎለት እንዲቀበልም ይጋብዘዋል።
  2. ሶላት ውስጥ አይኑን ወደ ሰማይ ከፍ ባደረገ ሰው ላይ ጠንካራ ክልከላና ከባድ ዛቻ መምጣቱን እንረዳለን።
  3. ዐውነል መዕቡድ ውስጥ እንዲህ ተብራርቷል: "የዚህ ምክንያትም ዓይኑን ወደ ሰማይ ከፍ ያደረገ ጊዜ ከቂብላ መስመር መውጣት፤ ሶላቱና አፈፃፀሙንም ችላ ማለት ስለሆነ ነው።"
  4. ሰላት ውስጥ ዓይንን ወደላይ ማንጋጠጥ ከተመስጦ ጋር ይቃረናል።
  5. የሶላት ጉዳይ የላቀ እንደሆነ እንረዳለን። ሰጋጅ የሆነ ሰውም ሶላት ውስጥ ከአላህ ጋር በተሟላ ስርዓት መቅረብ ግዴታው እንደሆነ እንረዳለን።

عرض الترجمات

39 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية