1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ዐቂዳ (እምነት)

حديث እኔ የማትጎዳና የማትጠቅም ድንጋይ መሆንህን አውቃለሁ። እኔ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሲስሙህ ባላይህ ኖሮ አልስምህም ነበር።

عَنْ عُمَرَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ:
أَنَّهُ جَاءَ إِلَى الحَجَرِ الأَسْوَدِ فَقَبَّلَهُ، فَقَالَ: إِنِّي أَعْلَمُ أَنَّكَ حَجَرٌ، لاَ تَضُرُّ وَلاَ تَنْفَعُ، وَلَوْلاَ أَنِّي رَأَيْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يُقَبِّلُكَ مَا قَبَّلْتُكَ.

ከዑመር (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና - እንደተላለፈው:
"ዑመር ወደ ጥቁሩ ድንጋይ (ሐጀሩል አስወድ) መጣና ሳመው። እንዲህም አለ: እኔ የማትጎዳና የማትጠቅም ድንጋይ መሆንህን አውቃለሁ። እኔ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሲስሙህ ባላይህ ኖሮ አልስምህም ነበር።"

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1597

المعنى الإجمالي

የአማኞች መሪ ዑመር ቢን ኸጧብ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና - በካዕባ ማእዘን ወደሚገኘው ጥቁር ድንጋይ መጣና ሳመው። እንዲህም አለ "እኔ የማትጎዳና የማትጠቅም ድንጋይ መሆንህን አውቃለሁ። እኔ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሲስሙህ ባላይህ ኖሮ አልስምህም ነበር።"

من فوائد الحديث

  1. ጦዋፍ የሚያደርጉ ሰዎች በሐጀረል አስወድ (በጥቁሩ ድንጋይ) በኩል ሲያልፉ በቀላሉ ለመሳም ከቻሉ መሳማቸው የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን።
  2. ጥቁሩን ድንጋይ በመሳም የሚፈለገው የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መከተል ነው።
  3. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ሀሳቡም ይህ ድንጋይ መጥቀምም ሆነ መጉዳትን አይችልም ነው። እንደማንኛውም እንደማይጎዱና እንደማይጠቅሙ ፍጡራን እርሱም የተፈጠረ ድንጋይ ነው። ዑመር ይህንን ንግግር በዚህ መድረክ ያሰራጨውም በሁሉም ሀገር ምስክር እንዲሆንና ከተለያዩ ሀገራት የተገኙ የሐጅ ሰዎች እንዲሸመድዱት ነው።"
  4. አምልኮ የተገደበ ነው። አላህና መልክተኛው ከደነገጉት ውጪ አይደነገግም።
  5. ጥበቡ ባይታወቅ እንኳ አምልኮዋ ትክክለኛ ከሆነች ትሰራለች። ሰዎች ትእዛዙን ተግባራዊ ማድረጋቸውና መታዘዛቸው ራሱ ከአምልኮ ዋነኛ ጥበቦች መካከል አንዱ ነውና።
  6. እንደ ድንጋይና ከርሱ ውጪ ያሉ መሰል ነገሮችን በሸሪዓ እስካልታዘዘ ድረስ በአምልኳዊ መንገድ እነርሱን መሳም መከልከሉን እንረዳለን።

عرض الترجمات

43 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية