1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ዐቂዳ (እምነት)

حديث አንተ የመጽሐፍ ባለቤት ወደሆኑ ህዝቦች ትሄዳለህ። ስለዚህም እነርሱ ዘንድ ስትደርስ ከአሏህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአሏህ መልዕክተኛ መሆናቸውን

عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا قَالَ:
قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ لِمُعَاذِ بْنِ جَبَلٍ، حِينَ بَعَثَهُ إِلَى الْيَمَنِ: «إِنَّكَ سَتَأْتِي قَوْمًا أَهْلَ كِتَابٍ، فَإِذَا جِئْتَهُمْ فَادْعُهُمْ إِلَى أَنْ يَشْهَدُوا أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ، وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللهِ، فَإِنْ هُمْ أَطَاعُوا لَكَ بِذَلِكَ، فَأَخْبِرْهُمْ أَنَّ اللهَ قَدْ فَرَضَ عَلَيْهِمْ خَمْسَ صَلَوَاتٍ فِي كُلِّ يَوْمٍ وَلَيْلَةٍ، فَإِنْ هُمْ أَطَاعُوا لَكَ بِذَلِكَ، فَأَخْبِرْهُمْ أَنَّ اللهَ قَدْ فَرَضَ عَلَيْهِمْ صَدَقَةً تُؤْخَذُ مِنْ أَغْنِيَائِهِمْ فَتُرَدُّ عَلَى فُقَرَائِهِمْ، فَإِنْ هُمْ أَطَاعُوا لَكَ بِذَلِكَ، فَإِيَّاكَ وَكَرَائِمَ أَمْوَالِهِمْ، وَاتَّقِ دَعْوَةَ الْمَظْلُومِ، فَإِنَّهُ لَيْسَ بَيْنَهُ وَبَيْنَ اللهِ حِجَابٌ».

ከኢብኑ ዐባስ ረዲየሏሁ ዐንሁማ እንደተላለፈው እንዲህ ብሏል፡
"የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሙዐዝ ቢን ጀበልን ወደ የመን በሚልኩበት ጊዜ እንዲህ አሉት፡ ' አንተ የመጽሐፍ ባለቤት ወደሆኑ ህዝቦች ትሄዳለህ። ስለዚህም እነርሱ ዘንድ ስትደርስ ከአሏህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአሏህ መልዕክተኛ መሆናቸውን ወደ መመስከር ጥሪ አድርግላቸው። እነሱ ለዚህ ጥሪህ ታዛዥ ከሆኑ አሏህ በነሱ ላይ በቀንና ምሽቱ ሁሉ አምስት ሶላቶችን ግዴታ እንዳደረገባቸው አሳውቃቸው። ለዚህ ጥሪህም ታዛዥ ከሆኑ አላህ በነሱ ላይ ከሀብታሞቻቸው ተይዞ ወደ ድሆቻቸው የምትሰጥ ምፅዋት ግዴታ እንዳደረገባቸው አሳውቃቸው። ለዚህ ጥሪህም ታዛዦች ከሆኑ አደራህን ውድ የሆኑ ንብረቶቻቸውን (ገንዘቦቻቸውን) ተጠንቀቅ! የተበዳይንም ልመና ተጠንቀቅ! እነሆ በሷና በአላህ መሀል ግርዶሽ የለምና።'"

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1496

المعنى الإجمالي

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሙዐዝ ቢን ጀበልን - ረዲየሏሁ ዐንሁ - ወደ አላህ መንገድ ተጣሪና አስተማሪ በማድረግ ወደ የመን በላኩበት ወቅት ከክርስቲያን የሆኑ ህዝቦችን ስለሚጋፈጥ እነርሱን በተመለከተ ዝግጁ እንዲሆን አሳሰቡት። ቀጥለውም ዳዕዋውን እጅግ አንገብጋቢ ከሆነው ነጥብ እንዲጀምር ነገሩት። መጀመርያ "ላ ኢላሃ ኢለሏህ ሙሐመዱን ረሱሉሏህ" ብለው በአሏህ አንድነትና በሙሐመድ መልዕክተኝነት በመመስከር እምነታቸውን እንዲያስተካክሉ ጥሪ እንዲያደርግ፤ ምክንያቱም ወደ እስልምና የሚገቡት በዚህ የምስክርነት ቃል ስለሆነ ነው። ይህንንም ተግባራዊ ካደረጉ ሶላትን እንዲሰግዱ ማዘዝ እንዳለበት ነገሩት። ምክንያቱም ከተውሒድ በኋላ ትልቁ ግዴታ ሶላት ስለሆነ ነው። ሶላትንም ካስተካከሉ በኋላ ከመካከላቸው ያሉት ባለ ፀጎች በመካከላቸው ላሉት ድሆች ከገንዘባቸው ዘካን እንዲያወጡ ማዘዝ እንዳለበት ነገሩት። ከዚያም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለዘካ ብሎ ከውድ ንብረታቸው እንዳይወስድ አስጠነቀቁት። ምክንያቱም የመስጠት ግዴታቸው ከመካከለኛ ንብረታቸው ነውና። ከዚያም የተበዳይ ዱዓእ ተቀባይነቱ ከፍተኛ በመሆኑ ተበዳይ ዱዓእ እንዳያደርግበት ግፍን መጠንቀቅ እንዳለበት አሳሰቡት።

من فوائد الحديث

  1. በ "ላ ኢላሀ ኢለሏህ" የመመስከር ትርጉም አሏህን በአምልኮ መነጠልና ከአሏህ ውጭ ምንንም አለማምለክ እንደሆነ እንረዳለን።
  2. ሙሐመድ የአሏህ መልዕክተኛ መሆናቸውን የመመስከር ትርጉሙ በሳቸውም ማመን፣ ይዘውት የመጡትንም እውነት ብሎ መቀበልና እሳቸው ወደ ሰው ልጆች ከተላኩት የመጨረሻው መልዕክተኛ መሆናቸውንም ማመን ነው።
  3. የእውቀት ባለቤት ወይም እርሱ ዘንድ ማምታቻ ያለውን ሰው ማናገር መሀይምን እንደማናገር አለመሆኑን፤ ለዚህም ነው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሙዓዝን "አንተ የመጽሐፍ ባለቤት ወደሆኑ ህዝቦች ትሄዳለህ።"በማለት የጠቆሙት።
  4. ሙስሊም በዲኑ ጉዳይ አወዛጋቢዎች ከሚያመጡት ማምታቻ መጥራት እንዲችል በእውቀት ላይ ሊሆን ይገባዋል። ይህም ዒልም በመፈለግ የሚሆን ነገር ነው።
  5. የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከተላኩ በኋላ የአይሁዶችና የክርስቲያኖች ሃይማኖት ውድቅ መሆኑንና በነቢያችን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አምነው ወደ እስልምና እስካልገቡ ድረስም ከሚድኑት ጎራ አለመሆናቸውን እንረዳለን።

عرض الترجمات

69 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
FR Français الفرنسية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
JA 日本語 اليابانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
KY Кыргызча القيرقيزية
NE नेपाली النيبالية
YO Yorùbá اليوروبا
LT Lietuvių الليتوانية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
SO Soomaali الصومالية
TG тоҷикӣ الطاجيكية
RW Kinyarwanda الكينياروندا
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
CS Čeština التشيكية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
FF Fulfulde الفولانية
IT Italiano الإيطالية
OM Oromoo الأورومو
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
BG Български البلغارية
AZ Azərbaycan الأذربيجانية
EL Ελληνικά اليونانية
AK Akan الأكانية
UZ O‘zbek الأوزبكية
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
LN Lingala اللينجالا
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
BM Bambara البامبارية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية
DA Dansk الدنماركية
RN Kirundi الكيروندي
KMR Kurmancî الكرمنجية
MS Bahasa Melayu الملايو