1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ዐቂዳ (እምነት)

حديث የምትናገረውና የምትጣራበት ጉዳይ መልካም ነው። ለሰራነው ፀያፍ ተግባር ማስማሪያ እንዳለው እንደው ብትነግረን?

عَنِ ‌ابْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اللهُ عَنْهُمَا:
أَنَّ نَاسًا مِنْ أَهْلِ الشِّرْكِ، كَانُوا قَدْ قَتَلُوا وَأَكْثَرُوا، وَزَنَوْا وَأَكْثَرُوا، فَأَتَوْا مُحَمَّدًا صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَقَالُوا: إِنَّ الَّذِي تَقُولُ وَتَدْعُو إِلَيْهِ لَحَسَنٌ، لَوْ تُخْبِرُنَا أَنَّ لِمَا عَمِلْنَا كَفَّارَةً، فَنَزَلَ {وَالَّذِينَ لا يَدْعُونَ مَعَ اللهِ إِلَهًا آخَرَ وَلا يَقْتُلُونَ النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللهُ إِلا بِالْحَقِّ وَلا يَزْنُونَ}[الفرقان: 68]، وَنَزَلَت: {قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَى أَنْفُسِهِمْ لا تَقْنَطُوا مِنْ رَحْمَةِ اللهِ} [الزمر: 53].

ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል:
"ከዚህ በፊት አብዝተው ነፍስ የሚገድሉ፣ አብዝተው ዝሙት የሚሰሩ የነበሩ የሺርክ ባለቤት የሆኑ ሰዎች ሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ በመምጣት እንዲህ አሉ ' የምትናገረውና የምትጣራበት ጉዳይ መልካም ነው። ለሰራነው ፀያፍ ተግባር ማስማሪያ እንዳለው እንደው ብትነግረን?' {እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይግገዙት፤ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ህግ የማይገድሉት፤ የማያመነዝሩትም ናቸው።} [ፉርቃን:68] የሚለውና {በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ።»} [አዝዙመር: 53] የሚለው አንቀፅ ወረደች።"

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ አልቡኻሪ - 4810

المعنى الإجمالي

ከሙሽሪኮች የሆኑ ሰዎች ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መጡ። አብዝተው የገደሉና ዝሙት የፈፀሙ ነበሩ። ለነቢዩ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: የምትጣራው ኢስላምና አስተምህሮቶቹ መልካም ጉዳይ ነው። ነገር ግን የወደቅንበት ሺርክና ከባድ ወንጀል ለርሱ ማስማሪያ አለውን?
ወንጀላቸው ከመብዛቱና ከመተለቁ ጋርም አላህ ከሰዎቹ ተውበታቸውን እንደተቀበለ የሚጠቁሙ ሁለት አንቀፆች ወረዱ። ይህ ባልነበር ኖሮ በክህደታቸውና ጥመታቸው ላይ ይቀጥሉ ነበር። ወደዚህ ሃይማኖትም አይገቡም ነበር።

من فوائد الحديث

  1. የኢስላም ትሩፋትና ልቅናውን እንረዳለን። ኢስላም ያለፈውን ወንጀል ያስምራል።
  2. አላህ በባሮቹ ላይ ያለው እዝነት ስፋቱን፣ ምህረቱንና ይቅር ባይነቱን እንረዳለን።
  3. የሺርክን ክልክልነት፣ ያለ ህግ ነፍስን የመግደልን ክልክልነት፣ የዝሙትን ክልክልነት፣ እነዚህን ወንጀሎች የሚዳፈር ላይ የመጣውንም ዛቻ እንረዳለን።
  4. ከኢኽላስና ከመልካም ስራ ጋር የተቆራኘ እውነተኛ ተውበት በአላህ መካድንም ጨምሮ ሁሉንም ትላልቅ ወንጀሎች ያስምራል።
  5. ከአላህ እዝነት ተስፋ መቁረጥ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።

عرض الترجمات

61 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
FR Français الفرنسية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
JA 日本語 اليابانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
KY Кыргызча القيرقيزية
NE नेपाली النيبالية
YO Yorùbá اليوروبا
LT Lietuvių الليتوانية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
SO Soomaali الصومالية
TG тоҷикӣ الطاجيكية
RW Kinyarwanda الكينياروندا
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
CS Čeština التشيكية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
IT Italiano الإيطالية
OM Oromoo الأورومو
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
AZ Azərbaycan الأذربيجانية
UZ O‘zbek الأوزبكية
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
BM Bambara البامبارية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية
KMR Kurmancî الكرمنجية