1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

حديث ሰዎች በአዛንና በመጀመሪያ ሰልፍ ያለውን ምንዳ ቢያውቁና እርሱንም እጣ ካልተጣጣሉ በቀር የማያገኙት ቢሆን ኖሮ እጣ ይጣጣሉ ነበር።

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضيَ اللهُ عنهُ أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«لَوْ يَعْلَمُ النَّاسُ مَا فِي النِّدَاءِ وَالصَّفِّ الْأَوَّلِ ثُمَّ لَمْ يَجِدُوا إِلَّا أَنْ يَسْتَهِمُوا عَلَيْهِ لَاسْتَهَمُوا، وَلَوْ يَعْلَمُونَ مَا فِي التَّهْجِيرِ لَاسْتَبَقُوا إِلَيْهِ، وَلَوْ يَعْلَمُونَ مَا فِي الْعَتَمَةِ وَالصُّبْحِ لَأَتَوْهُمَا وَلَوْ حَبْوًا».

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦
"ሰዎች በአዛንና በመጀመሪያ ሰልፍ ያለውን ምንዳ ቢያውቁና እርሱንም እጣ ካልተጣጣሉ በቀር የማያገኙት ቢሆን ኖሮ እጣ ይጣጣሉ ነበር። (ወደ መስጊድ) ማልዶ የመሄድን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ ለርሱ ይሽቀዳደሙ ነበር። የዒሻና ሱብሒን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ እየዳኹም ቢሆን ይመጡ ነበር።"

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ ሙስሊም - 437

المعنى الإجمالي

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሰዎች በአዛንና በመጀመሪያ ሰልፍ የሚገኘውን ደረጃ፣ መልካምና በረከት ቢያውቁ ኖሮና ከዚያም ለመቀደምና ቅድሚያ ለማግኘት ማነው የሚገባው ለሚለው እጣ መጣጣል ቢጠበቅባቸው ኖሮ እጣ ይጣጣሉ ነበር። ወደ ሶላት በመጀመሪያ ወቅት ቀድሞ የመሄድንም ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ ይሽቀዳደሙ ነበር። ወደ ዒሻ ሶላትና ወደ ፈጅር ሶላት መስጂድ የመምጣት ምንዳ መጠኑን ቢያውቁ ኖሮና ወደ መስጂድ መምጣት ቀላል ባይሆንላቸው ኖሮ ህፃን ልጅ እየዳኸ እንደሚመጣው በጉልበታቸው እየዳኹም ይመጡ ነበር አሉ።

من فوائد الحديث

  1. የአዛን ደረጃ መገለፁ፤
  2. ወደ ኢማም መቅረብና የመጀመሪያ ሰልፍ ያለው ደረጃ መገለፁ፤
  3. ሶላት ለመስገድ ተወዳጅ በሆነው በመጀመሪያ ወቅት ወደ መስጂድ ቀድሞ መሄድ ያለው ደረጃ መገለፁን እንረዳለን። ይህም ትልቅ ደረጃ ስላለውና እርሱን ተከትሎ በርካታ ጥቅሞች ስለሚገኝ ነው። ከነዚህ ጥቅሞች መካከልም: የመጀመሪያን ሰልፍ ማግኘት፤ ሶላት ላይ ከመጀመሪያ ጀምሮ መድረስ፤ ሱናን መስገድ፤ ቁርአን መቅራት፤ መላእክቶች ለርሱ ምህረት ይጠይቁለታል፤ ሶላት እስኪደርስ እስከተጠባበቀ ድረስም ሶላት ላይ ከመሆን አለመወገድን፤ ከዚህም ውጪ ያሉ ጥቅሞችን ያገኛል።
  4. እነዚህን ሁለት ሶላቶች በህብረት ለመስገድ በመገኘት ላይ መነሳሳቱንና በዚህም ብዙ ትሩፋት እንደሚገኝ እንረዳለን። ይህ ብዙ ትሩፋት የሚገኘውም በመጀመሪያ ወቅትና በመጨረሻው ወቅት ያለውን የእንቅልፍ ሰአት በማደፍረሱ ነፍስን ስለሚከብዳት ነው። ስለዚህም በሙናፊቆች ላይ ከባዳቹ ሶላቶች እነርሱ ሆኑ።
  5. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ በሚያጨቃጭቅና ሰው በሚበዛበት ሐቆች ላይ እጣ መጣጣል እንደሚቻል ያፀድቅልናል።"
  6. ሁለተኛው ሰልፍ ከሶስተኛው፣ ሶስተኛው ደግሞ ከአራተኛው ሰልፍ ይበልጣል።

عرض الترجمات

40 اللغة
EN English الإنجليزية
ID Indonesia الإندونيسية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية