1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

حديث ሐጅና ዑምራን አከታትላችሁ አድርጉ። ወናፍ የብረትን፣ የወርቅንና የብርን ቆሻሻ እንደሚያስወግደው እነርሱም ድህነትንና ወንጀልን ያስወግዳሉ። ተቀባይነት ላለው ሐጅ ከጀነት በቀር ሌላ ምንም ምንዳ የለውም።

عَنْ عَبْدِ اللهِ بْنِ مَسْعُودٍ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«تَابِعُوا بَيْنَ الحَجِّ وَالعُمْرَةِ، فَإِنَّهُمَا يَنْفِيَانِ الفَقْرَ وَالذُّنُوبَ كَمَا يَنْفِي الكِيرُ خَبَثَ الحَدِيدِ، وَالذَّهَبِ، وَالفِضَّةِ، وَلَيْسَ لِلْحَجَّةِ الْمَبْرُورَةِ ثَوَابٌ إِلاَّ الجَنَّةُ».

ከዓብደላህ ቢን መስዑድ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
"ሐጅና ዑምራን አከታትላችሁ አድርጉ። ወናፍ የብረትን፣ የወርቅንና የብርን ቆሻሻ እንደሚያስወግደው እነርሱም ድህነትንና ወንጀልን ያስወግዳሉ። ተቀባይነት ላለው ሐጅ ከጀነት በቀር ሌላ ምንም ምንዳ የለውም።"»

ሶሒሕ ነው። رواه الترمذي والنسائي وأحمد ሱነን ቲርሚዚ - 810

المعنى الإجمالي

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የሐጅና የዑምራን አምልኮ አቀራርቦ በመፈፀምና ከቻሉ ሳያቆራርጡ በመፈፀም ላይ አነሳሱ። ምክንያቱንም ሲገልፁ ብረትን በወናፍ እሳት መንፋት ብረቱ ላይ የተቀላቀለውን ባዕድ የማዕድን ቆሻሻ ለማስወገድ ምክንያት እንደሆነው ሁሉ እነርሱንም መፈፀም ድህነትንና ወንጀልን እንዲሁም ወንጀል በቀልብ ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖ ለማስወገድ ምክንያት መሆናቸውንም ገለፁ።

من فوائد الحديث

  1. ሐጅና ዑምራን የማከታተል ትሩፋትና በርሱም ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  2. ሐጅና ዑምራን ማከታተል የሀብትና ወንጀልን የማስማር ሰበብ እንደሆነ እንረዳለን።
  3. ሙባረክ ፉሪ እንዲህ ብለዋል: "(ድህነትን ያስወግዳሉ።) በማለት የተፈለገው በእጅ በሚገኝ ሀብት የሚወገደውን ውጫዊውን ድህነትም ሊሆን ይችላል። የቀልብ መብቃቃትን በማግኘት የሚወገደውን ውስጣዊ ድህነትም ሊሆን ይችላል።"

عرض الترجمات

34 اللغة
EN English الإنجليزية
ID Indonesia الإندونيسية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية