1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ዐቂዳ (እምነት)

حديث ላንተ የተመኘኸውንም ከርሱም ጋር የርሱን አምሳያ ሌላም ይሰጥሃል።

عَن أَبِي هُرَيْرَةَ رَضيَ اللهُ عنهُ عَنْ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِنَّ أَدْنَى مَقْعَدِ أَحَدِكُمْ مِنَ الْجَنَّةِ أَنْ يَقُولَ لَهُ: تَمَنَّ فَيَتَمَنَّى، وَيَتَمَنَّى، فَيَقُولُ لَهُ: هَلْ تَمَنَّيْتَ؟ فَيَقُولُ: نَعَمْ، فَيَقُولُ لَهُ: فَإِنَّ لَكَ مَا تَمَنَّيْتَ وَمِثْلَهُ مَعَهُ».

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦
«ጀነት ውስጥ የአንዳችሁ ትንሹ ደረጃ አላህ ለርሱ "ተመኝ" ይለዋል። እርሱም ደጋግሞ ይመኛል። አላህም ለርሱ "ተመኘህን?" ይለዋል። እርሱም "አዎን" ይላል። አላህም ይለዋል: "ላንተ የተመኘኸውንም ከርሱም ጋር የርሱን አምሳያ ሌላም ይሰጥሃል።"»

ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ ሙስሊም - 182

المعنى الإجمالي

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጀነት ለገባ ሰው የሚሰጠው ትንሹና ዝቅተኛው ደረጃና ስፍራ አላህ ለርሱ እንዲህ ይለዋል: "ተመኝ" ከሚመኘው ሁሉ አንድም ነገር ሳያስቀር ይጠቅሳል። ደጋግሞም ይመኛል። አላህም ለርሱ እንዲህ ይለዋል: "ተመኘህን?" እርሱም "አዎን" ይላል። አላህም "የተመኘኸውንና ከተመኘኸው ጋር የርሱን አምሳያ ሌላም ይሰጥሃል።" ይለዋል።

من فوائد الحديث

  1. የጀነት ሰዎች ደረጃ እንደሚበላለጥ እንረዳለን።
  2. የአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ቸርነት ትልቅ መሆኑ መገለፁን እንረዳለን።
  3. የጀነት ፀጋ በውስን ነገር ላይ አይገደብም። ይልቁንም አንድ አማኝ ጀነት ውስጥ የተመኘውንና ነፍሱ የፈለገችውን ሁሉ ያገኛል። ይህም ከአላህ በሆነ ችሮታ፣ ቸርነትና ደግነት ነው።

عرض الترجمات

43 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية