1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

حديث ከባህር ውሃ ጋር ብትቀላቀል የባህሩን ውሃ የምታበላሽ የሆነችን ንግግር ተናገርሽ።" አሏት።

عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ المؤْمنينَ رَضيَ اللهُ عنها قَالَت:
قُلْتُ لِلنَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: حَسْبُكَ مِنْ صَفِيَّةَ كَذَا وَكَذَا، -قَالَ أَحدُ الرُّوَاةِ: تَعْنِي قَصِيرَةً- فَقَالَ: «لَقَدْ قُلْتِ كَلِمَةً لَوْ مُزِجَتْ بِمَاءِ الْبَحْرِ لَمَزَجَتْهُ» قَالَتْ: وَحَكَيْتُ لَهُ إِنْسَانًا، فَقَالَ: «مَا أُحِبُّ أَنِّي حَكَيْتُ إِنْسَانًا وَأَنَّ لِي كَذَا وَكَذَا».

ከአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች:
«ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለሰፊያ (ነውር’ኮ) እንዲህ እንዲህ ነገሯ ራሱ ይበቃሃል። አልኳቸው። (አንዱ የሐዲሥ ዘጋቢ እንዲህ እንዲህ ነገሯ ይበቃሃል በማለት የፈለገችው እጥረቷን ነው ብለዋል።) እርሳቸውም "ከባህር ውሃ ጋር ብትቀላቀል የባህሩን ውሃ የምታበላሽ የሆነችን ንግግር ተናገርሽ።" አሏት። "እንዲህም አለች "ለርሳቸው የሆነ ሰው የሚያደርገውን አስመስዬ በድርጊት አሳየኃቸው።" እርሳቸውም "ለኔ እንዲህ እንዲህ ቢሰጠኝ እንኳ ሰውን ማስመሰል አያስደስተኝም (አልወድም)።" አሉ።»

ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል። ሱነን አቡዳውድ - 4875

المعنى الإجمالي

የአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "ከሶፊያ‘ኮ (የፈለገችውም የአማኞች እናትን ነው) ከአካላዊ ነውሮቿ እርሷ አጭር መሆኗ ይበቃሃል።" አለቻቸው። እርሳቸውም "ከባህር ውሃ ጋር ብትቀላቀል ውሃውን አሸንፋ የምትለውጠውንና የምታበላሸውን ንግግር ተናገርሽ።" አሏት። እንዲህም አለች "የሆነን ሰው ዝቅ በማድረግ መልኩ የሚሰራውን ስራ አምሳያ አስመስዬ ሰራሁላቸው።" ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "ነውሩን መናገር ወይም የሚሰራውን ስራ አስመስዬ በመስራቴ ወይም የሚናገረውን አምሳያ በመናገሬ ለዚህ ተግባር ከዱንያ እጅግ በርካታ ነገር ቢሰጠኝ ራሱ ማድረጉ አያስደስተኝም።" አሉ።

من فوائد الحديث

  1. ከሀሜት መከልከሉና መስፈራራቱን ተረድተናል።
  2. በማሳነስና ዝቅ በማድረግ መልኩ ሰዎችን ማስመሰልና የነርሱን ሁኔታ መከተል ከተከለከለው ሀሜት ይመደባል።
  3. አካላዊ ነውሮችን መግለፅ የሀሜት አንድ ክፍል ነው።
  4. ቃዲ እንዲህ ብለዋል: «"መዝጅ" ማለት ሌላን ነገር ወደርሱ መቀላቀል፣ መለወጥ ማለት ነው። ሀሳቡም ይህ ሀሜት ባህር ውስጥ የሚቀላቀል ቢሆን ኖሮ የባህሩ ውሃ ከመብዛቱም ጋር ውሃውን ይለውጠው ነበር ማለት ነው። ጥቂት ተግባራት ቢቀላቀልበትስ ምን ሊሆን ይችል?»
  5. በሚስቶች መካከል የሚከሰት ቅናት መጠቀሱን እንመለከታለን።
  6. ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ውግዝ ተግባርን አለማፅደቃቸው።
  7. ዱንያና ውስጧ ያሉ ነገሮች ከአላህ ውዴታና ከአላህ አለመቆጣት ጋር ሲነፃፀሩ ያነሱ መሆናቸውን እንረዳለን።
  8. እስልምና ክብሮች በንግግርም ሆነ በተግባር እንዳይደፈሩ በመከልከል ክብር እንዲጠበቅ ያዘዘ የመልካም ስነምግባር ሃይማኖት ነው። ምክንያቱም ክብርን መንካት በሙስሊሞች መካከል ጠላትነትንና ጥላቻን የሚፈጥር ነውና።

عرض الترجمات

43 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية