1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ዐቂዳ (እምነት)

حديث ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'አላህ ዘንድ እጅግ ትልቁ ወንጀል ምንድነው?' ብዬ ጠየቅኩ። እርሳቸውም 'አላህ ፈጥሮህ ሳለ ለርሱ ቢጤን ማድረግክ ነው።

عَنْ عَبْدِ اللهِ بنِ مَسْعُودٍ رضي الله عنه قال:
سَأَلْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: أَيُّ الذَّنْبِ أَعْظَمُ عِنْدَ اللهِ؟ قَالَ: «أَنْ تَجْعَلَ لِلهِ نِدًّا وَهُوَ خَلَقَكَ» قُلْتُ: إِنَّ ذَلِكَ لَعَظِيمٌ، قُلْتُ: ثُمَّ أَيُّ؟ قَالَ: «وَأَنْ تَقْتُلَ وَلَدَكَ؛ تَخَافُ أَنْ يَطْعَمَ مَعَكَ» قُلْتُ: ثُمَّ أَيُّ؟ قَالَ: «أَنْ تُزَانِيَ حَلِيلَةَ جَارِكَ».

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦
"ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'አላህ ዘንድ እጅግ ትልቁ ወንጀል ምንድነው?' ብዬ ጠየቅኩ። እርሳቸውም 'አላህ ፈጥሮህ ሳለ ለርሱ ቢጤን ማድረግክ ነው።' አሉ። እኔም 'ይህማ ትልቅ ነው።' አልኩኝ። 'ከዚያስ ቀጥሎ' አልኳቸው። እርሳቸውም 'ልጅህን ከአንተ ጋር መብላቱን ፈርተህ መግደልክ ነው።' አሉኝ። 'ከዚያስ ቀጥሎ' አልኳቸው። እርሳቸውም 'በጎረቤትህ ሚስት ላይ ዝሙት መስራትህ ነው።' አሉኝ።"

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ አልቡኻሪ - 4477

المعنى الإجمالي

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለ እጅግ ትልቁ ወንጀል ተጠየቁ: እጅግ ትልቁ ወንጀል ትልቁ ሺርክ ነው። እርሱም ለአላህ በተመላኪነቱ ወይም በጌትነቱ ወይም በስሞቹና ባህሪያቶቹ ምሳሌ ወይም ቢጤን ማድረግክ ነው። ይህን ወንጀል አላህ ያለ ተውበት አይምረውም። ባለቤቱ በዚህ ወንጀል ላይ ሳለ ከሞተም በእሳት ውስጥ ዘውታሪ ነው። ቀጥሎም ሰውዬው ልጁን ከርሱ ጋር መብላቱን ፈርቶ መግደሉ ነው። በመሰረቱ ነፍስን መግደል ክልክል ነው። ነገር ግን ተገዳዩ የገዳዩ ዘመድ ከሆነ ወንጀሉ የከፋ ይሆናል። አሁንም በድጋሚ ገዳዩ የመግደሉ አላማ ተገዳዩ በአላህ ሲሳይ ላይ እንዳይጋራው አስቦ ከሆነ ወንጀሉ እጅግ የከፋ ይሆናል። ቀጥሎ አንድ ሰው በጎረቤቱ ሚስት ላይ ዝሙት መስራቱ ነው። እርሷ ላይ ዝሙት እስኪሰራና ታዛዡ እስክትሆን ድረስ የጎረቤቱን ሚስት ለማታለል መሞከሩ ነው። በመሰረቱ ዚና ክልክል ነው። ነገር ግን ዝሙት የተሰራባት ሸሪዓ ለነርሱ መልካም እንድንውልላቸው፣ በጎ እንድናደርግላቸውና ጥሩ ወዳጅነት እንዲኖረን ያዘዘን በሆኑት የጎረቤት ሚስት ከሆነች ወንጀሉ የከፋ ይሆናል።

من فوائد الحديث

  1. መልካም ስራዎች በደረጃ እንደሚበላለጡት ሁሉ ወንጀሎችም በከባድነታቸው ይበላለጣሉ።
  2. እጅግ ትልቁ ወንጀል በአላህ ማጋራት ነው። ቀጥሎ ከአንተ ጋር መብላቱን በመፍራት ልጅን መግደል ነው። ቀጥሎም በጎረቤት ሚስት ላይ ዝሙት መፈፀም ነው።
  3. ሲሳይ በአላህ እጅ ነው። ጥራት የተገባው አላህ በፍጡራን ሲሳይ ላይ ኃላፊነቱን ወስዷል።
  4. የጎረቤት ሐቅ ታላቅ መሆኑንና ጎረቤትን የማወክ ወንጀልነቱ ሌላን አካል ከማወክ የበለጠ እጅግ የከፋ ወንጀል መሆኑን እንረዳለን።
  5. ፈጣሪ ብቸኛው ለአምልኮ የተገባና አጋር የሌለው ነው።

عرض الترجمات

60 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
FR Français الفرنسية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
JA 日本語 اليابانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
KY Кыргызча القيرقيزية
NE नेपाली النيبالية
YO Yorùbá اليوروبا
LT Lietuvių الليتوانية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
SO Soomaali الصومالية
TG тоҷикӣ الطاجيكية
RW Kinyarwanda الكينياروندا
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
CS Čeština التشيكية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
OM Oromoo الأورومو
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
AZ Azərbaycan الأذربيجانية
UZ O‘zbek الأوزبكية
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
BM Bambara البامبارية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية
KMR Kurmancî الكرمنجية