1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

حديث የሽማግሌ ቀልብ ለሁለት ነገሮች ወጣት ከመሆን አይወገድም: (እነርሱም) ዱንያን በመውደድና ምኞትን በማርዘም ነው።

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«لاَ يَزَالُ قَلْبُ الكَبِيرِ شَابًّا فِي اثْنَتَيْنِ: فِي حُبِّ الدُّنْيَا وَطُولِ الأَمَلِ».

ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦
"የሽማግሌ ቀልብ ለሁለት ነገሮች ወጣት ከመሆን አይወገድም: (እነርሱም) ዱንያን በመውደድና ምኞትን በማርዘም ነው።"

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል። ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6420

المعنى الإجمالي

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሽማግሌ ሰውነቱ ቢጃጅና ቢደክምም ቀልቡ ግን ሁለት ነገሮችን በመውደድ በኩል ወጣት መሆኗን ተናገሩ: የመጀመሪያው: ገንዘብን በማብዛት ዱንያን መውደድ ነው። ሁለተኛው: ረጅም ህይወትን፣ እድሜን፣ ምቾትና ምኞትን መውደድ ነው።

من فوائد الحديث

  1. የሰው ልጅ የተፈጠረበት ባህሪው መገለፁ፤ ይሀውም ዱንያን መውደድና ምኞትን ማርዘም ነው።
  2. ምኞትን ማርዘምና ገንዘብ ማጠራቀም ላይ መጓጓት የተወገዘ መሆኑ መጠቆሙ፤ ይህም ለሞት መዘጋጀትን እንደሚገባ፤ ሀብታም የሆነ ሰው ሶደቃ መስጠቱ ያለው ደረጃ፣ ድሃ የሆነ ሰው ደግሞ መብቃቃቱ ያለውን ደረጃ መረዳት እንደሚገባ ያስፈርዳል።
  3. የሰው ልጅ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ነገር ነፍሱ ናት። ምንግዜም እንድትቆይለት ይፈልጋል። ስለዚህም እድሜው መርዘሟን ወደደ፤ ጤንነቱና መደሰቻዎቹ እንዲዘወትሩለት የሚያደርገው ትልቁ ምክንያት ደሞ ገንዘብ ስለሆነ ገንዘብንም ወደደ፤ ጉዳዩ በቅርቡ እንደሚያጣው በተሰማው ልክ ውዴታውና እንዲዘወትርለት ያለው ፍላጎትም በዛው ልክ ይበረታል።

عرض الترجمات

35 اللغة
EN English الإنجليزية
ID Indonesia الإندونيسية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية