1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ዐቂዳ (እምነት)

حديث አንድ ሰው ሌላን ሰው በአመፀኝነትም ሆነ በከሃዲነት አያነውረውም ባለቤቱ እንደዚያ ካልሆነ ወደርሱ ብትመለስ እንጂ።

عَنْ أَبِي ذَرٍّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ أَنَّهُ سَمِعَ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«لاَ يَرْمِي رَجُلٌ رَجُلًا بِالفُسُوقِ، وَلاَ يَرْمِيهِ بِالكُفْرِ، إِلَّا ارْتَدَّتْ عَلَيْهِ، إِنْ لَمْ يَكُنْ صَاحِبُهُ كَذَلِكَ».

ከአቡዘር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምተዋል:
"አንድ ሰው ሌላን ሰው በአመፀኝነትም ሆነ በከሃዲነት አያነውረውም ባለቤቱ እንደዚያ ካልሆነ ወደርሱ ብትመለስ እንጂ።"

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6045

المعنى الإجمالي

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለሌላ ሰው "አንተ አመፀኛ" ወይም "አንተ ከሃዲ" ያለ ሰው ያ ሰው እንደተናገረው ካልሆነና ለተጠቀሰው ባህሪ የተገባ ካልሆነ ንግግሩ ወደራሱ የሚመለስ መሆኑን አስጠነቀቁ። እንደተናገረው ከሆነ ግን በተናገረው ንግግር እውነተኛ ስለሆነ አንድም ነገር ወደርሱ አይመለስበትም።

من فوائد الحديث

  1. ያለ ሸሪዓዊ ተጨባጭ ማረጋገጫ ሰዎችን በክህደት ወይም በአመፀኝነት ማነወር ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
  2. በሰዎች ላይ በሚሰጡ ፍርዶች ማረጋገጥ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
  3. ኢብኑ ደቂቅ አልዒድ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ከሙስሊሞች መካከል አንድን ሰው እርሱ ከሃዲ ሳይሆን ከሃዲ ለሚል ሰው ትልቅ ዛቻ ነው። ይህም ትልቅ ጣጣ ነው።"
  4. ኢብኑ ሐጀር አልዓስቀላኒይ እንዲህ ብለዋል: «ነገር ግን በዚህ ንግግሩ እውነቱን ከሆነ አመፀኛ ወይም ከሃዲ አይሆንም ሲባል "አንተ አመፀኛ" በሚለው ንግግሩ ምንም ወንጀለኛ ሊሆን አይችልም የሚለውን አያሲዝም። ይልቁንም ይህ ሁኔታ በዝርዝር መታየት ይገባዋል። "አንተ አመፀኛ" ሲለው የፈለገበት እርሱን መምከር ወይም የርሱን ሁኔታ ለሌሎች በመግለፅ ሌሎችን መምከር ከሆነ ይፈቀዳል። እርሱን ማነወር፣ ወንጀል መስራቱ እንዲታወቅ ለማድረግና ለመጉዳት ብቻ አስቦ ከሆነ ግን አይፈቀድም። ምክንያቱም እርሱ የታዘዘው እንዲሸሽግለት፣ በመልካም መልኩ እንዲያስተምረውና እንዲመክረው ነው። ይህንን በልስላሴ ማስተማር እስከቻለ ድረስ በሀይል መፈፀሙ አይፈቀድለትም። በሀይል መምከሩ አብዛኛው ሰው እልህ ውስጥ ገብቶ እንደሚያደርገው እንዲጠምና በዛ ወንጀል ላይ እንዲዘወትር ምክንያት ይሆናልና። በተለይ አዛዡ ከታዛዡ በደረጃ ዝቅ ያለ የሆነ ጊዜ ይህ ይከሰታል።»

عرض الترجمات

49 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
NE नेपाली النيبالية
LT Lietuvių الليتوانية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
TG тоҷикӣ الطاجيكية
RW Kinyarwanda الكينياروندا
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
OM Oromoo الأورومو
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية