1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

حديث አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመምጣት "አስሰላሙ ዐለይኩም" አላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱለት። ቀጥሎም ተቀመጠ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "አስር" አሉ።

عَنْ عِمْرَانَ بْنِ حُصَيْنٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ:
جَاءَ رَجُلٌ إِلَى النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَقَالَ: السَّلَامُ عَلَيْكُمْ، فَرَدَّ عَلَيْهِ ثُمَّ جَلَسَ، فَقَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «عَشْرٌ» ثُمَّ جَاءَ آخَرُ فَقَالَ: السَّلَامُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللَّهِ، فَرَدَّ عَلَيْهِ فَجَلَسَ، فَقَالَ: «عِشْرُونَ» ثُمَّ جَاءَ آخَرُ فَقَالَ: السَّلَامُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللَّهِ وَبَرَكَاتُهُ، فَرَدَّ عَلَيْهِ فَجَلَسَ، فَقَالَ: «ثَلَاثُونَ».

ከዒምራን ቢን ሑሶይን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመምጣት "አስሰላሙ ዐለይኩም" አላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱለት። ቀጥሎም ተቀመጠ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "አስር" አሉ። ቀጥሎም ሌላ ሰውዬ መጣና "አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏህ" አላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱለት። እርሱም ተቀመጠ። እርሳቸውም "ሀያ" አሉ። ቀጥሎም ሌላ ሰውዬ መጣና "አስሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱሏሂ ወበረካቱህ" አላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱለት። እርሱም ተቀመጠ። እርሳቸውም "ሰላሳ" አሉ።»

ሐሰን ነው። رواه أبو داود والترمذي وأحمد والدارمي ሱነን አቡዳውድ - 5195

المعنى الإجمالي

አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመምጣት (አስሰላሙ ዐለይኩም) አላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱለት። ቀጥሎም ተቀመጠ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለርሱ አስር ምንዳ ተጽፎለታል አሉ። ከዚያም ሌላ ሰው መጣና (አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏህ) አላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱለትና ተቀመጠ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለርሱ ሀያ ምንዳ አለው አሉ። ከዚያም ሌላ ሰውዬ መጣና (አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱህ) አላቸው። ሰላምታውን መለሱለትና ተቀመጠ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለርሱ ሰላሳ ምንዳ አለው አሉ። ማለትም እያንዳንዱ ቃል አስር ምንዳ ያስገኛል ማለታቸው ነው።

من فوائد الحديث

  1. የሚመጣ (ከውጪ የሚገባ) ሰው ለተቀመጡ ሰዎች ሰላምታን በማቅረብ ይጀምራል።
  2. የሰላምታ ቃላቶች በጨመሩ ቁጥር ምንዳም እንደሚጨምር እንረዳለን።
  3. ሰላምታን ለማቅረብ የተሟላው ሰላምታ (አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱህ) የሚለው ነው። ሰላምታን ለመመለስም በላጩ ቃል (ወዐለይኩሙ‐ስሰላም ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱህ) የሚለው ነው።
  4. ሰላምታን የማቅረብና የመመለስ ደረጃዎች እንደሚበላለጡና ምንዳውም እንደሚበላለጥ እንረዳለን።
  5. ሰዎችን መልካም ማስተማርና የተሻለውን እንዲያስገኙም ማስገንዘብ እንደሚገባ እንረዳለን።
  6. ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ሰላምታን ጀማሪው (ወረሕመቱሏህ) የሚለውን ቃል ከጨመረ መላሹ (ወበረካቱህ) የሚለውንም መጨመሩ ይወደድለታል፤ ሰላምታን ጀማሪው (ወበረካቱህ) የሚለውን ቢጨምር ግን መላሹ ሌላ ቃል መጨመር ይደነገግለታልን? ልክ እንደዚሁ ሰላምታን ጀማሪው (ወበረካቱህ) የሚለው ቃል ላይ ሌላ ቃል መጨመር ይደነገግለታልን? ኢማሙ ማሊክ ሙወጦእ በተሰኘው መፅሀፋቸው "ሰላምታ እስከ በረከት (ወበረካቱህ) ድረስ ይጠናቀቃል።" የሚለውን ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ዘግበዋል።"

عرض الترجمات

43 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية