1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

حديث ወንጀልም ሆነ ዝምድና መቁረጥ የሌለበትን ዱዓ የሚያደርግ አንድም ሙስሊም የለም በዛች ዱዓው ምክንያት አላህ ከሶስት ነገሮች አንዱን የሚሰጠው ቢሆን እንጂ: ወይ የለመነው በፍጥነት ይሰጠዋል ፤ ወይ ልመናው ለመጪው ዓለም መልካም ምንዳ ማደለቢያ ይሆንለታል፤ ወይም የለመነውን ጉዳይ የሚያክል መጥፎ ነገር ከሱ ዞር ያስደርግለታል። " ሶሀቦችም " ስለዚህ (ዱዓእ) እናብዛ?" አሉ። እሳቸውም "(ዱዓእ ካበዛችሁ) የአላህ ስጦታም እጅግ ይበዛል።" አሏቸው።

عَنْ أَبِي سَعِيدٍ رضي الله عنه أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَا مِنْ مُسْلِمٍ يَدْعُو بِدَعْوَةٍ لَيْسَ فِيهَا إِثْمٌ، وَلَا قَطِيعَةُ رَحِمٍ، إِلَّا أَعْطَاهُ اللهُ بِهَا إِحْدَى ثَلَاثٍ: إِمَّا أَنْ تُعَجَّلَ لَهُ دَعْوَتُهُ، وَإِمَّا أَنْ يَدَّخِرَهَا لَهُ فِي الْآخِرَةِ، وَإِمَّا أَنْ يَصْرِفَ عَنْهُ مِنَ السُّوءِ مِثْلَهَا» قَالُوا: إِذنْ نُكْثِرُ، قَالَ: «اللهُ أَكْثَرُ».

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦
«ወንጀልም ሆነ ዝምድና መቁረጥ የሌለበትን ዱዓ የሚያደርግ አንድም ሙስሊም የለም በዛች ዱዓው ምክንያት አላህ ከሶስት ነገሮች አንዱን የሚሰጠው ቢሆን እንጂ: ወይ የለመነው በፍጥነት ይሰጠዋል ፤ ወይ ልመናው ለመጪው ዓለም መልካም ምንዳ ማደለቢያ ይሆንለታል፤ ወይም የለመነውን ጉዳይ የሚያክል መጥፎ ነገር ከሱ ዞር ያስደርግለታል። " ሶሀቦችም " ስለዚህ (ዱዓእ) እናብዛ?" አሉ። እሳቸውም "(ዱዓእ ካበዛችሁ) የአላህ ስጦታም እጅግ ይበዛል።" አሏቸው።»

ሶሒሕ ነው። አሕመድ ዘግበውታል። ሙስነድ አሕመድ - 11133

المعنى الإجمالي

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንድ ሙስሊም ወንጀልና በደል ለመፈፀም እንዲገራለት መለመንን የመሰለ ወንጀል ባልሆነ፤ በቅርብ ዘመዱና በልጆቹ ላይ እርግማን መለመንን የመሰለ ዝምድና መቁረጥ ባልሆነ ዱዓእ አላህን የለመነና የጠየቀ ጊዜ አላህ በዱዓው አማካይነት ከሶስት ነገሮች አንዱን ይሰጠዋል ብለው ተናገሩ፡ ወይ የለመነውን በፍጥነት ይሰጠዋል፤ ወይም የትንሳኤ ቀን ደረጃውን ከፍ እንዲያደርግለት ወይም እንዲታዘንለትና ወንጀሉን መማሪያ እንዲሆንለት አላህ ምንዳውን ያደልብለታል፤ ወይም የለመነውን የሚያክል የሆነ መጥፎን ነገር በዱንያው ውስጥ ይከላከልለታል። ሶሐቦችም ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "ስለዚህ ከነዚህ ደረጃዎች አንዱን እንድናገኝ ዱዓን እናብዛ እንዴ?" አሉ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "አላህ ዘንድ ያለው እናንተ ከምትጠይቁትም በላይ ትልቅና ብዙ ነው። የርሱ ስጦታ አያልቅምም አይቀንስምም።" አሏቸው።

من فوائد الحديث

  1. የሙስሊም ዱዓ የማትመለስ ተቀባይነት ያላት ናት። ነገር ግን ይህ መስፈርቶቿና ስነስርዓቷ የተሟላ ጊዜ ነው። ስለዚህም አንድ ባሪያ አብዝቶ ዱዓ ማድረግ እንጂ የዱዓውን ውጤት በፍጥነት ለማግኘት መቸኮል የለበትም።
  2. የዱዓ ተቀባይነት ማግኘት የፈለግነውን በማግኘት ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም። በዱዓው አማካይነት ወንጀሉን ሊምረው ወይም መጪው ዓለም ላይ ሊያደልብለትም ይችላልና።
  3. ኢብኑ ባዝ እንዲህ ብለዋል: "ችክ ብሎ ዱዓ ማድረግ፣ በአላህ ላይ ጥሩ እሳቤን ማሳደርና ተስፋ አለመቁረጥ ዱዓ ተቀባይነትን እንዲያገኝ ከሚያደርጉ ትላልቅ ምክንያቶች መካከል ናቸው። ስለዚህም ሰውዬው ዱዓውን ችክ ብሎ ሊያደርግ፤ በአላህ ላይ ያለው እሳቤን ሊያሳምር፤ አላህ ጥበበኛና አዋቂ እንደሆነ በማወቅ ለአንዳች ጥበብ ሲባል ዱዓውን መቀበልን ሊያፈጥን ለአንዳች ጥበብም ዱዓውን መቀበሉን ሊያዘገይ እንደሚችል መረዳት ይገባል። አላህ ጠያቂ ከጠየቀው የተሻለ ነገርም ይሰጣል።"

عرض الترجمات

45 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
NE नेपाली النيبالية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية