1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

حديث 'አሁን ላይ እኔ ያላየኋቸው ሁለት አይነት የእሳት ባለቤቶች አሉ። (እነሱም) ሰዎችን የሚደበድቡበት እንደከብት ጭራ የመሰለ አለንጋ ያላቸው ሰዎች እና ለብሰው የተራቆቱ የሆኑ ራሳቸው ተዘንብለው ሌሎችን ለክፉ የሚጋብዙ፤ ጭንቅላታቸው እንደተዘነበለ የግመል ሻኛ የሆነ ሴቶች ናቸው።

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«صِنْفَانِ مِنْ أَهْلِ النَّارِ لَمْ أَرَهُمَا، قَوْمٌ مَعَهُمْ سِيَاطٌ كَأَذْنَابِ الْبَقَرِ يَضْرِبُونَ بِهَا النَّاسَ، وَنِسَاءٌ كَاسِيَاتٌ عَارِيَاتٌ مُمِيلَاتٌ مَائِلَاتٌ، رُؤُوسُهُنَّ كَأَسْنِمَةِ الْبُخْتِ الْمَائِلَةِ، لَا يَدْخُلْنَ الْجَنَّةَ، وَلَا يَجِدْنَ رِيحَهَا، وَإِنَّ رِيحَهَا لَيُوجَدُ مِنْ مَسِيرَةِ كَذَا وَكَذَا».

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
'አሁን ላይ እኔ ያላየኋቸው ሁለት አይነት የእሳት ባለቤቶች አሉ። (እነሱም) ሰዎችን የሚደበድቡበት እንደከብት ጭራ የመሰለ አለንጋ ያላቸው ሰዎች እና ለብሰው የተራቆቱ የሆኑ ራሳቸው ተዘንብለው ሌሎችን ለክፉ የሚጋብዙ፤ ጭንቅላታቸው እንደተዘነበለ የግመል ሻኛ የሆነ ሴቶች ናቸው። እነዚህ ጀነት አይገቡም፤ መዓዛዋንም አያገኙም። የጀነት ሽታዋም (እነሱ ካሉበት) የሆነ ያክል ርቆ ይገኛል።'"

ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ ሙስሊም - 2128

المعنى الإجمالي

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁለት አይነት ሰዎች የእሳት ባለቤቶች እንደሆኑና በሳቸው ዘመን እንዳላዩዋቸውና እንደሌሉ፤ በተቃራኒው ከርሳቸው ህልፈት በኋላ እንደሚመጡ ተናገሩ።
የመጀመሪያው አይነት ሰዎች: ሰዎችን የሚመቱበት የከብት ጭራ የሚያክል አለንጋ ይዘው የሚዞሩ ሰዎች ናቸው። እነርሱም ሰዎችን ያለ አግባብ በመምታት የግፈኞች ተባባሪ የሆኑ ፖሊሶች ናቸው።
ሁለተኛው አይነት ሰዎች ደግሞ: በተለምዶ የሴቶች ተፈጥሮ የሆነውን የጥብቅነትንና አይነ አፋርነትን ልብስ ያወለቁ ሴቶች ናቸው።
በተጨባጭ ገላቸው ላይ ልብስ ያለ ቢሆንም በትክክለኛው ግን የተራቆቱ ናቸው። ምክንያቱም እነሱ ቆዳቸውን ግልፅ ለማውጣት ሰውነትን የሚያሳይ ቀጭን ልብስ ነውና የሚለብሱት፤ (ወይ) ውበታቸውን ለማጉላት የተወሰነ ሰውነታቸውን ሸፍነው የተወሰነውን የገለጡ ናቸውና በማለት እነዚህን ሴቶች ገለጿቸው። በአለባበሳቸውና በአረማመዳቸው የወንዶችን ቀልብ ወደነርሱ እንዲያዘነብል የሚያደርጉ፣ ትከሻዎቻቸውንም የሚያወዛውዙ፣ ሌሎችንም እነርሱ ወደ ወደቁበት ጥመት እንዲያዘነብሉ የሚያደርጉ ናቸው። ከነዚህ ሴቶች ባህሪ መካከልም: ጭንቅላታቸው ያዘነበለ የግመል ሻኛ ይመስላል። የፀጉራቸውን መጠን በማሰሪያና በመሳሰሉት በማሰር ያተልቋታል። በግመል ሻኛ የተመሳሰሉት ፀጉራቸውና ጉንጉናቸው ከጭንቅላታቸው በላይ ከፍ ስለሚልና የግመል ሻኛ እንደሚዘነበለው ፀጉራቸውን በሚጎነጎኑት ሳቢያ ወደአንድ ጎን እስኪዘነበል ድረስ ሰበር ስለሚል ነው። ይህን ባህሪ የተላበሱ ሴቶች እነርሱ ላይ ይህ ከባድ ዛቻ አለባቸው። እርሱም ጀነት ላይገቡ፣ ሽታዋንም ላያገኙ፣ ወደርሷም ላይቀርቡ ነው። የጀነት መዓዛ ከሩቅ ስፍራ ነው የሚሸተው።

من فوائد الحديث

  1. ሰዎችን ወንጀል ሳይሰሩ ወይም ኃጢአት ሳይተገብሩ መምታትና ማወክ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
  2. ግፈኞችን በግፋቸው ላይ ማገዝ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
  3. ሴቶች ከመገላለጥ፣ ከመራቆት፣ ሀፍረተ ገላን ከሚገልፅ ወይም ቅርፅን ከሚያሳይ ጠባብና ስስ ልብስ መጠንቀቅ እንዳለባቸው።
  4. ሙስሊም ሴቶች የአላህን ትእዛዝ አጥብቀው በመያዝ ላይና አላህን ከሚያስቆጣውና በመጨረሻው ዓለም አሳማሚና ዘውታሪ ቅጣት እንዲገባቸው ከሚያደርጓቸው ነገር እንዲርቁ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  5. ይህ ሐዲሥ የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ነቢይነት ከሚጠቁሙ ሐዲሦች አንዱ ነው። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) (በህይወት ዘመናቸው) ያልተከሰተ ሩቅ ጉዳይን ተናገሩ እንደተናገሩትም ተከሰተ።

عرض الترجمات

57 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
KY Кыргызча القيرقيزية
NE नेपाली النيبالية
YO Yorùbá اليوروبا
LT Lietuvių الليتوانية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
SO Soomaali الصومالية
TG тоҷикӣ الطاجيكية
RW Kinyarwanda الكينياروندا
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
CS Čeština التشيكية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
IT Italiano الإيطالية
OM Oromoo الأورومو
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
AZ Azərbaycan الأذربيجانية
UZ O‘zbek الأوزبكية
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية
KMR Kurmancî الكرمنجية