1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ዐቂዳ (እምነት)

حديث ወደ ቅናቻ የተጣራ ሰው የተከተሉትን ሰዎች አምሳያ ምንዳ ያገኛል። ይህም (ለርሱ የሚሰጠው ምንዳ) ከምንዳቸው አንዳች ሳይቀነስ ነው።

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَنْ دَعَا إِلَى هُدًى كَانَ لَهُ مِنَ الْأَجْرِ مِثْلُ أُجُورِ مَنْ تَبِعَهُ، لَا يَنْقُصُ ذَلِكَ مِنْ أُجُورِهِمْ شَيْئًا، وَمَنْ دَعَا إِلَى ضَلَالَةٍ كَانَ عَلَيْهِ مِنَ الْإِثْمِ مِثْلُ آثَامِ مَنْ تَبِعَهُ، لَا يَنْقُصُ ذَلِكَ مِنْ آثَامِهِمْ شَيْئًا».

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
"ወደ ቅናቻ የተጣራ ሰው የተከተሉትን ሰዎች አምሳያ ምንዳ ያገኛል። ይህም (ለርሱ የሚሰጠው ምንዳ) ከምንዳቸው አንዳች ሳይቀነስ ነው። ወደ ጥመት የተጣራ ሰውም የተከተሉትን ሰዎች አምሳያ ወንጀል ይኖርበታል። ይህም (በርሱ ላይ የሚኖረው ወንጀል) ከወንጀሎቻቸው ምንም ሳይቀነስ ነው።"

ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ ሙስሊም - 2674

المعنى الإجمالي

በንግግሩ ወይም በተግባሩ እውነትና መልካም ወዳለበት መንገድ ሰዎችን የመራ፣ የጠቆመና የቀሰቀሰ ሰው የተከታዩን አምሳያ ምንዳ እንደሚያገኝና ይህም ከተከታዩ ምንዳ አንዳችም ሳይቀነስ እንደሆነ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገለፁ። በንግግር ወይም በተግባር ወንጀልና ኃጢአት ወይም የማይፈቀድ ነገር ወዳለበት የጥመትና የክፋት መንገድ ሰዎችን የጠቆመ ሰውም የተከታዩን አምሳያ ወንጀልና ኃጢአት ይኖርበታል። ይህም ከነርሱ ወንጀል አንዳችም ሳይቀነስ ነው።

من فوائد الحديث

  1. በትንሹም ሆነ በብዛት ወደ ቅናቻ መጣራት ያለውን ደረጃ እንረዳለን። ተጣሪ ሰው በርሱ ጥሪ የሰሩ ሰዎችን ምንዳ አምሳያ ይኖረዋል። ይህም የአላህን ትልቅ ችሮታና ሙሉ ቸርነት ያስረዳናል።
  2. በትንሹም ሆነ በብዛት ወደ ጥመት የመጣራትን አደጋ እንረዳለን። ወደ ጥመት የሚጣራም ሰው በሰበካው የሰራን ሰው ወንጀል አምሳያ በርሱ ላይ ይኖርበታል።
  3. ምንዳ የሚሰጠው በስራው አይነት እንደሆነ እንረዳለን። ወደ መልካም የተጣራ ሰው በጥሪው የሰራን ሰው ምንዳ አምሳያ ለርሱ ይኖረዋል። ወደ መጥፎ የሰበከ ሰውም በሰበካው የሰራን ሰው ወንጀል አምሳያ በርሱ ላይ ይኖርበታል።
  4. አንድ ሙስሊም ወንጀልን ግልፅ በማድረጉ ሰዎች አይተው እንዳይከተሉት መጠንቀቅ አለበት። በዚህ ላይ ሆን ብሎ ባይቀሰቅስ እንኳ በተከተሉት ሰዎች ልክ ወንጀል ላይ ይወድቃልና።

عرض الترجمات

58 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
KY Кыргызча القيرقيزية
NE नेपाली النيبالية
YO Yorùbá اليوروبا
LT Lietuvių الليتوانية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
SO Soomaali الصومالية
TG тоҷикӣ الطاجيكية
RW Kinyarwanda الكينياروندا
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
CS Čeština التشيكية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
OM Oromoo الأورومو
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
AZ Azərbaycan الأذربيجانية
UZ O‘zbek الأوزبكية
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
BM Bambara البامبارية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية
KMR Kurmancî الكرمنجية