1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ዐቂዳ (እምነት)

حديث ጀናዛ (ሬሳ) ቃሬዛ ላይ የተቀመጠች ጊዜና ሰዎች ትከሻቸው ላይ የተሸከሟት ጊዜ ሬሳዋ መልካም ከሆነች "ቀደም አድርጉኝ!" ትላለች።

عَن أَبِي سَعِيدٍ الخُدْرِيَّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِذَا وُضِعَتِ الجِنَازَةُ وَاحْتَمَلَهَا الرِّجَالُ عَلَى أَعْنَاقِهِمْ فَإِنْ كَانَتْ صَالِحَةً قَالَتْ: قَدِّمُونِي، وَإِنْ كَانَتْ غَيْرَ صَالِحَةٍ قَالَتْ: يَا وَيْلَهَا أَيْنَ يَذْهَبُونَ بِهَا؟ يَسْمَعُ صَوْتَهَا كُلُّ شَيْءٍ إِلَّا الإِنْسَانَ، وَلَوْ سَمِعَهُ صَعِقَ».

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"ጀናዛ (ሬሳ) ቃሬዛ ላይ የተቀመጠች ጊዜና ሰዎች ትከሻቸው ላይ የተሸከሟት ጊዜ ሬሳዋ መልካም ከሆነች "ቀደም አድርጉኝ!" ትላለች። መልካም ካልሆነች ደግሞ "ወዬውላት የት ነው ይዛችኋት የምትሄዱት?" ትላለች። ከሰው በቀር ያለ ነገር ሁሉ ድምጿን ይሰማል። የሰው ልጅ ቢሰማው ኖሮ ራሱን ስቶ ይወድቅ ነበር።"

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል። ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1314

المعنى الإجمالي

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጀናዛ ቃሬዛ ላይ የተቀመጠ ጊዜና ሰዎችም ትከሻቸው ላይ የተሸከሟት ጊዜ መልካም ከሆነች ከፊት ለፊቷ ፀጋዎችን ስለምትመለከት "ቀደም አድርጉኝ!" ትላለች። መልካም ካልሆነች ደግሞ ከፊት ለፊቷ ቅጣትን ስለምትመለከት በሚያወግዝ ድምፅ "ወይ ጥፋቷ! የት ነው ይዛችኋት የምትሄዱት?!" ትላለች። ከሰው በቀር ሁሉ ነገር ድምጿን ይሰማታል። ሰው ቢሰማው ኖሮ የሚሰማው ነገር ከባድ ከመሆኑ የተነሳ ራሱን ይስት ነበር አሉ።

من فوائد الحديث

  1. መልካም ሆኖ የሞተ ሰው ከመቀበሩ በፊት ብስራቶችን ይመለከታል። ከሀዲ ግን ትዕግስት ያጣል። ከዚህ በተቃራኒ የሆነን ነገርም ይመለከታል።
  2. አንዳንድ ድምጾች ከሰው በቀር ያሉ ፍጡራን ይሰሙታል። የሰው ልጅ ግን ሊሰማው አይችልም።
  3. ጀናዛን የመሸከም ሱናው ወንዶች በትከሻዎቻቸው ላይ መሸከማቸው ነው፤ ሴቶችን አይመለከትም። ምክንያቱም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሴቶች ጀናዛን መከተላቸውን ስለከለከሏቸው ነው።

عرض الترجمات

45 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
YO Yorùbá اليوروبا
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية