1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

حديث ሁለት ሴት ልጆችን እስኪደርሱ ድረስ የተንከባከበ ሰው የትንሳኤ ቀን እኔና እሱ እንዲህ ሆነን ይመጣል።" ጣታቸውንም አጣበቁ።

عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَنْ عَالَ جَارِيَتَيْنِ حَتَّى تَبْلُغَا جَاءَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَنَا وَهُوَ» وَضَمَّ أَصَابِعَهُ.

ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፦
"ሁለት ሴት ልጆችን እስኪደርሱ ድረስ የተንከባከበ ሰው የትንሳኤ ቀን እኔና እሱ እንዲህ ሆነን ይመጣል።" ጣታቸውንም አጣበቁ።»

ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ ሙስሊም - 2631

المعنى الإجمالي

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሁለት ሴት ልጆችን ወይም እህቶችን የተለገሰና ለአቅመ ሄዋን እስኪደርሱ ድረስም ለነርሱ ቀለባቸውን፣ በመልካም ማነፁን፣ ወደ መልካም መጠቆሙን፣ ከመጥፎ መከልከሉንና የመሳሰሉትን ሀላፊነቶች እየተወጣ የተንከባከባቸው ሰው የትንሳኤ ቀን እርሱና ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንደዚ ሆነን ይመጣል ብለው መጠቆሚያ ጣታቸውንና መሀል ጣታቸውንም አጣብቀው አሳዩ።

من فوائد الحديث

  1. ሴት ልጆች እስኪያገቡ ወይም እስኪደርሱ ድረስ የቀለባቸውንና በመልካም የማነፁን ሀላፊነት የተወጣ ሰው ምንዳው ትልቅ መሆኑን እንረዳለን። ለእህቶችም ማድረግ ተመሳሳይ ነው።
  2. የሴት ልጆች ፍላጎትን ማሟላት የወንድ ልጆችን ፍላጎት ከማሟላት የበለጠ ምንዳ ያስገኛል። ወንድ ልጆችን በተመለከተ ይህን መሰል ምንዳ አልተጠቀሰምና። ይህም የሆነበት ምክንያት የሴት ልጆች ቀለብና ለነርሱ ጉዳይ ትኩረት መስጠት ከወንድ ልጆች የበለጠ ስለሆነ ነው። ሴት ልጆች እንደወንዶች ጉዳያቸውን በራሳቸው የማያስፈፅሙና የተሸሸጉ ስለሆኑ፤ በተጨማሪም አባቶች በወንድ ልጆች እንደሚሳቡት በሴት ልጆቻቸው ግን በጠላቶቻቸው ላይ ስለማይታገዙባቸው፣ የአባቶችን ስም ህያው በማድረግ፣ ዘሩን በማስቀጠልና በመሳሰሉት በኩል እምብዛም ስለሆኑ የአባቶችን ፍላጎት የሚስቡ አይደሉም። በዚህም ሰበብ በነርሱ ላይ ወጪን የሚያወጣው ሰው ኒያውን ከማሳመር ጋር መታገሱና ስራውን ለአላህ ማጥራቱ ይበልጥ አስፈላጊ ሆነ። በዚህም ምንዳው ገዝፎለት የትንሳኤ ቀንም የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጓደኛ መሆን ቻለ።
  3. ሴት ልጅ የመድረሷ ምልክቶች: አስራ አምስት አመት መሙላቷ ወይም አስራ አምስት አመት ባትሞላም የወር አበባ ማየቷ ወይም የብልት አካባቢ ፀጉር ማውጣቷ ወይም በተኛችበት የዘር ፈሳሽ ማየቷ ናቸው።
  4. ቁርጡቢይ እንዲህ ብለዋል: «"እስኪደርሱ" በማለት የሚፈለገው ራሷን የምትችልበት ደረጃ እስክትደርስ ማለት ነው። ይህም የሚሆነው (ትዳር ይዘው) ባሎቻቸው ዘንድ ሲገቡ ነው። እስክትደርስ በማለት የተፈለገው የወር አበባ እስክታይና በሸሪዓ ግዴታዎች ተጠያቂ እስክትሆን ማለት አይደለም። የወር አበባ ከማየቷ በፊት አግብታም በባሏ ቀላቢ ከመፈለግ ልትብቃቃ ትችላለች። የወር አበባ ማየት ጀምራም ራሷን እንድትችል ብትተው በምትጠፋና ሁኔታዋ በሚበላሽ መልኩ ላይ ልትሆን ትችላለችና። እንደውም በዚህ ሁኔታ ላይ ስትሆን እንክብካቤዋ ተሟልቶ ለጋብቻ እንድትፈለግ ጥበቃ፣ ቁጥጥርና እንክብካቤ የበለጠ የምትፈልግበት ወቅት ነው። ለዚህም ሲባል ዑለማዎቻችን እንዲህ ብለዋል: ከሴት ልጅ ወላጅ ላይ ልጁ አቅመ ሄዋን በመድረሷ ብቻ ቀለብ አይቀርለትም። ሀላፊነቱ የሚነሳው ባሏ ጋር በመግባቷ ነው።

عرض الترجمات

51 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
NE नेपाली النيبالية
YO Yorùbá اليوروبا
LT Lietuvių الليتوانية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
TG тоҷикӣ الطاجيكية
RW Kinyarwanda الكينياروندا
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
OM Oromoo الأورومو
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية