1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

حديث በላጩን ሥራችሁ፣ ንጉሳችሁ ዘንድ የጠራችውን ሥራችሁ፣ ደረጃችሁንም ከፍ የምታደርገውን ስራችሁን፣

عَنْ أَبِي الدَّرْدَاءِ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«أَلاَ أُنَبِّئُكُمْ بِخَيْرِ أَعْمَالِكُمْ، وَأَزْكَاهَا عِنْدَ مَلِيكِكُمْ، وَأَرْفَعِهَا فِي دَرَجَاتِكُمْ وَخَيْرٌ لَكُمْ مِنْ إِنْفَاقِ الذَّهَبِ وَالوَرِقِ، وَخَيْرٌ لَكُمْ مِنْ أَنْ تَلْقَوْا عَدُوَّكُمْ فَتَضْرِبُوا أَعْنَاقَهُمْ وَيَضْرِبُوا أَعْنَاقَكُمْ؟» قَالُوا: بَلَى. قَالَ: «ذِكْرُ اللهِ تَعَالَى».

ከአቡ ደርዳእ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ:
"በላጩን ሥራችሁ፣ ንጉሳችሁ ዘንድ የጠራችውን ሥራችሁ፣ ደረጃችሁንም ከፍ የምታደርገውን ስራችሁን፣ ለናንተ ወርቅና ብር ከመመፅወት የሚበልጥላችሁን ስራ፣ ጠላቶቻችሁን ተገናኝታችሁ አንገታቸውን ከምትመቱበት አንገታችሁን ከሚመቱበት ስራችሁም በላጩ የሆነውን ስራ አልነግራችሁምን?" ሶሐቦችም "እንዴታ!" አሉ። እርሳቸውም "አላህን ማውሳት ነው።" አሉ።»

ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል። ሱነን ቲርሚዚ - 3377

المعنى الإجمالي

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባልደረቦቻቸውን እንዲህ በማለት ጠየቁ
ልዕለ ኃያሉ ንጉስ አላህ ዘንድ በላጩን፣ የላቀውን፣ የፋፋውን፣ የፀዳውንና የጠራውን ስራችሁን እንድነግራችሁ ትፈልጋላችሁን
ጀነት ውስጥም ያለውን ደረጃችሁን ከፍ የሚያደርግላችሁን ስራስ ማወቅ ትፈልጋላችሁ?
ወርቅና ብር ከመመፅወትም ለናንተ የሚበልጥላችሁን?
ከከሀዲያን ጋር ለውጊያ ተገናኝታችሁ አንገቶቻቸውን ከምትቀሉና አንገቶቻችሁንም ከሚቀሉ የሚበልጠውን ስራ ማወቅ ትፈልጋላችሁን?
ሶሐቦችም: አዎ ይህንን ማወቅ እንፈልጋለን አሉ።
ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁሉም ወቅትና በአጠቃላይ ሁኔታዎች ላይ አላህን ማውሳት ነው አሏቸው።

من فوائد الحديث

  1. በይፋም ይሁን በድብቅ አላህን ማውሳት ማዘውተር ከትላልቅ መቃረቢያዎችና አላህ ዘንድ እጅግ ጠቃሚ ከሆኑት ነው።
  2. ሁሉም ስራዎች የተደነገጉት አላህን ማውሳትን ለማቋቋም (ተፈፃሚ ለማድረግ) ነው። አላህ እንዲህ ብሏል: {ሶላትንም (በእርሷ) እኔን ለማውሳት ስገድ።} ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል "በአላህ ቤት ዙሪያ ጦዋፍ ማድረግ፣ በሶፋና መርዋ መካከል መሮጥ፣ ጠጠር መወርወር ሁሉ የተደረገው አላህን ማውሳት ለማቋቋም ነው።" አቡዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል።
  3. ዒዝ ቢን ዐብዱሰላም (ቀዋዒድ) በሚባለው መጽሐፋቸው ውስጥ እንዲህ ብለዋል "ይህ ሐዲሥ ምንዳ ሁሉም አምልኮዎች ላይ በልፋት ልክ እንደማይመጣ ከሚጠቁሙ ሐዲሦች አንዱ ነው። አንዳንዴ አላህ በትንሽ ስራ በትልቁ ስራ ከሚመነዳው በላይ ይመነዳል። ምንዳ የስራ ደረጃዎች በልቅና በሚበላለጡት ልክ ይበላለጣል።"
  4. መናዊ "ፈይዱል ቀዲር" በሚባለው መጽሐፋቸው ውስጥ እንዲህ አሉ: ይህ ሐዲሥ የሚተረጎመው ንግግሩ ከቀረበላቸው ሰዎች አንፃር ነው ዚክር በላጭ የሚሆነው በሚል ነው። ነቢዩ ያናገሩት ሰው በውጊያ ብቃቱ እስልምና የሚጠቀምበትን አንበሳ ጀግና ሰው ቢሆን ኖሮ ለርሱ በላጩ ስራ ጂሀድ ይሉት ነበር። ወይም በገንዘቡ ድሀዎች የሚጠቀሙበትን ሀብታም ቢሆን ኖሮ ያናገሩት ለርሱ በላጩ ስራ ሶደቃ ይሉት ነበር። ሐጅ የሚችልን ሰው ያናገሩ ቢሆን ኖሮ ሐጅ ይሉት ነበር። ወይም ወላጆች ያሉትን ቢያናግሩ ኖሮ እነሱን መንከባከብ ይሉት ነበር። ሐዲሦቹ የሚስማሙት በዚህ መንገድ ነው።
  5. የተሟላው ዚክር ልቦና እያስተነተነው ምላስ የተናገረው ዚክር ነው። ቀጥሎም በልብ ብቻ የተፈፀመ ዚክር ነው ተፈኩርን ይመስል። ቀጥሎ በምላስ ብቻ የተፈፀመ ነው። በሁሉም ግን ኢንሻ አሏህ ምንዳ ይገኝባቸዋል።
  6. አንድ ሙስሊም ከሁኔታዎች ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ዚክሮች እንደ ንጋትና ምሽት ዚክሮች፣ ወደ መስጂድ፣ ቤት፣ ሽንት ቤት ሲገባና ሲወጣ የሚባሉትን ዚክሮችና ሌሎችንም አዘውትሮ መፈፀሙ አላህን በብዙ ከሚያመወሱት መካከል ያደርገዋል።

عرض الترجمات

57 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
KY Кыргызча القيرقيزية
NE नेपाली النيبالية
YO Yorùbá اليوروبا
LT Lietuvių الليتوانية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
SO Soomaali الصومالية
TG тоҷикӣ الطاجيكية
RW Kinyarwanda الكينياروندا
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
CS Čeština التشيكية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
OM Oromoo الأورومو
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
AZ Azərbaycan الأذربيجانية
UZ O‘zbek الأوزبكية
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية
KMR Kurmancî الكرمنجية