عَنِ الحُسَينِ بنِ عَلِيٍّ بنِ أَبِي طَالِبٍ رضي الله عنهما قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«الْبَخِيلُ مَنْ ذُكِرْتُ عِنْدَهُ فَلَمْ يُصَلِّ عَلَيَّ».

ከሑሰይን ቢን ዐሊይ ቢን አቢጧሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"ስስታም ማለት እርሱ ዘንድ ተወስቼ በኔ ላይ ሶላት ያላወረደ ነው።"»

ሶሒሕ ነው። رواه الترمذي والنسائي في الكبرى وأحمد አስሱነኑል ኩብራ ነሳኢ - 8046

المعنى الإجمالي

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የርሳቸውን ስም ወይም ቅጥያ ስም ወይም ባህሪያቸውን በሚሰማ ወቅት እርሳቸው ላይ ሶላት ማውረድ የተወን ሰው አስጠነቀቁ። እንዲህም አሉ: ስስታምነቱ የተሟላ ስስታም ማለት እርሱ ዘንድ ተወስቼ ሶለዋት ያላወረደብኝ ነው። ይህም የሆነው ከሚከተሉት ጉዳዮች አንፃር ነው:
የመጀመሪያው: ሶለዋት በማውረዱ ምክንያት ትንሽም ይሁን ብዙ የማይከስርበት፣ ገንዘብ የማያወጣበት፣ ጉልበቱን የማያፈስበት በሆነ ነገር ላይ መሰሰት ስለሆነ፤
ሁለተኛው: በአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ ሶለዋት ባለማውረዱ በርሳቸው ላይ ሶላት የማውረድን ምንዳ በነፍሱ ላይ ስለሳሳና ስለነፈጋት ነው። በርሳቸው ላይ ሶለዋት ባለማውረዱ ትእዛዝን ለመተግበርና ምንዳን ለማግኘት ሊፈፅመው ግዴታ የሆነበትን ሐቅ ከመፈፀም ታቅቧልም ሰስቷልም።
ሶስተኛው: በርሳቸው ላይ ሶለዋት ማውረድ የተወሰነውን የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሐቅ መወጣት ነው። ያስተማሩን፣ ያቀኑን፣ ወደ አላህ ተባረከ ወተዓላ የጠሩን፣ ይህንን ወሕይና ሸሪዓ ይዘው የመጡልን እርሳቸው ናቸው። ከአላህ ተባረከ ወተዓላ በኋላ የመመራታችን ምክንያት እርሳቸው ናቸው። በርሳቸው ላይ ሶለዋት ያላወረደ ሰው በርግጥም በነፍሱ ላይም ስስታም ሆኗል። ለነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ካላቸው ሐቆች መካከል በትንሹ ሐቅ እንኳ ስስታም ሆኗል።

من فوائد الحديث

  1. በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ ሶለዋት ማውረድን መተው የስስታምነት ቁንጮ ነው።
  2. በማንኛውም ወቅት በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ ሶለዋት ማውረድ በላጭ ከሆኑ አምልኮዎችና መቃረቢያዎች መካከል ነው። እርሳቸው በሚወሱበት ወቅት ደሞ በላጭነቱ ጠንከር ይላል።
  3. ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: «በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ ሶለዋት ሲያወርድ ሶለዋትና ሰላምን ሰብስቦ ይበል። በአንዱ ላይ ብቻ አይቆጠብ። (ሶለላሁ ዐለይሂ) ብቻ ወይም (ዐለይሂ ሰላም) ብቻ አይበል።»
  4. {አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ ሶላትን ያወርዳሉ።} በሚለው የአላህ ቃል ዙሪያ አቡል ዐሊያህ እንዲህ ብለዋል: «አላህ በነቢዩ ላይ ሶለዋት አወረደ ማለት እርሳቸውን ማወደሱ ነው። ሶለዋት ከመላእክትና ከሰው ሲሆን ደግሞ ዱዓእ ነው።»
  5. ሐሊሚይ እንዲህ ብለዋል: (አላሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመድ) የሚለው ትርጉም አላህ ሆይ! በዱንያ መወሳታቸውን ከፍ በማድረግ፣ ሃይማኖታቸውን የበላይ በማድረግ፣ ሸሪዓቸውን ዘውታሪ በማድረግ አላቃቸው። በመጪው አለም ደግሞ ለኡመታቸው አማላጅ በማድረግ፣ ምንዳቸውንና አጅራቸውን በማተለቅ፣ ለመጀመሪያውም ሆነ ለመጨረሻው ፍጡር በምስጉኑ ስፍራ ደረጃቸውን በመግለፅ፣ አላህ ፊት ምስክር ከሆኑ ቅርቦች ባጠቃላይ በማስቀደም አላቃቸው ማለት ነው።

عرض الترجمات

51 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
KY Кыргызча القيرقيزية
NE नेपाली النيبالية
LT Lietuvių الليتوانية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
TG тоҷикӣ الطاجيكية
RW Kinyarwanda الكينياروندا
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
OM Oromoo الأورومو
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية