1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

حديث ወደኔ ተወዳጅ የሆነውና የትንሳኤ ቀንም መቀመጫው ወደኔ ቅርብ የሚሆነው መልካም ስነምግባር ያለው ነው።

عَنْ جَابِرٍ رَضيَ اللهُ عنهُ أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِنَّ مِنْ أَحَبِّكُمْ إِلَيَّ وَأَقْرَبِكُمْ مِنِّي مَجْلِسًا يَوْمَ القِيَامَةِ أَحَاسِنَكُمْ أَخْلاَقًا، وَإِنَّ أَبْغَضَكُمْ إِلَيَّ وَأَبْعَدَكُمْ مِنِّي مَجْلِسًا يَوْمَ القِيَامَةِ الثَّرْثَارُونَ وَالمُتَشَدِّقُونَ وَالمُتَفَيْهِقُونَ»، قَالُوا: يَا رَسُولَ اللهِ، قَدْ عَلِمْنَا الثَّرْثَارُونَ وَالمُتَشَدِّقُونَ فَمَا الْمُتَفَيْهِقُونَ؟ قَالَ: «الْمُتَكَبِّرُونَ».

ከጃቢር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፡
«"ወደኔ ተወዳጅ የሆነውና የትንሳኤ ቀንም መቀመጫው ወደኔ ቅርብ የሚሆነው መልካም ስነምግባር ያለው ነው። ወደኔ የተጠላውና የትንሳኤ ቀንም መቀመጫው ከኔ እጅግ የራቀው እውነትን ለመቀልበስ እየተጣጣረ የሚያወራ፤ ለአንደበተ ርቱእነት ንግግር የሚያበዛና ሙተፈይሂቆች ናቸው።" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እውነትን ለመቀልበስ እየተጣጣረ የሚያወራንና ለአንደበተ ርቱዕነት ንግግር የሚያበዛን አውቀናል። መተፈይሂቆች እነማን ናቸው?" አሉ። እርሳቸውም "ኩራተኞች ናቸው።" አሉ።»

ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚ ዘግበውታል። ሱነን ቲርሚዚ - 2018

المعنى الإجمالي

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ: ዱንያ ውስጥ ወደኔ ተወዳጁ፤ የትንሳኤ ቀንም መቀመጫው ወደኔ ቅርብ የሆነው ስነምግባሩ ያማረ ነው። ዱንያ ውስጥ ወደኔ የተጠላው የትንሳኤ ቀንም መቀመጫው ከኔ የራቀው መጥፎ ስነምግባር ያለው፤ (ሠርሣሮች) ከእውነት ለመውጣት ከአቅሙ በላይ እየተጣጣረ ንግግር የሚያበዛ፤ (ሙተሸዲቆች) ያለምንም ጥንቃቄ አንደበተ ርቱዕ ለመባልና ንግግሩን ለማላቅ ንግግሩን የሚያሰፋ፤ እና (ሙተፈይሂቆች) ናቸው። ሶሐቦችም የአላህ መልክተኛ ሆይ! "ሠርሣሮች" እና "ሙተሸዲቆች"ን አውቀናል። "ሙተፈይሄቆች" ማን ናቸው? አሉ። እርሳቸውም: "ኩራተኞች፣ ንግግራቸውን በማስፋትና በንግግራቸው አፋቸውን በመክፈት በሰዎች ላይ የሚያፌዙ ናቸው።" አሉ።

من فوائد الحديث

  1. መልካም ስነምግባር የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ውዴታንና የትንሳኤ ቀን ወደርሳቸው መቅረብን ከሚያመጡ ምክንያቶች መካከል አንዱ ነው።
  2. መልካም ስነምግባር ሰዎች እርስ በርሳቸው እንዲዋደዱ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል አንዱ ነው። መጥፎ ስነምግባር ደግሞ በተቃራኒ ነው።
  3. ስነምግባርን በማሳመር፤ በመተናነስ፣ ጨካኝ ባለመሆንና ያለአቅም ባለመጣጣር ላይ መነሳሳቱን ተረድተናል።
  4. ማብዛትን፣ ኩራትን፣ ልቆ መታየትን፣ ከአቅም በላይ መጣጣርን አስቦ ከመናገር መከልከሉን እንረዳለን።

عرض الترجمات

44 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية