1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

حديث የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት በሚከፍቱበት ወቅትና

عَن ابْنِ عُمَرَ رضي الله عنهما:
أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ كَانَ يَرْفَعُ يَدَيْهِ حَذْوَ مَنْكِبَيْهِ إِذَا افْتَتَحَ الصَّلَاةَ، وَإِذَا كَبَّرَ لِلرُّكُوعِ، وَإِذَا رَفَعَ رَأْسَهُ مِنَ الرُّكُوعِ، رَفَعَهُمَا كَذَلِكَ أَيْضًا، وَقَالَ: «سَمِعَ اللَّهُ لِمَنْ حَمِدَهُ، رَبَّنَا وَلَكَ الحَمْدُ»، وَكَانَ لاَ يَفْعَلُ ذَلِكَ فِي السُّجُودِ.

ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው:
«የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት በሚከፍቱበት ወቅትና ለሩኩዕ ተክቢራ በሚያደርጉ ጊዜ እጃቸውን በትከሻቸው ትይዩ ከፍ ያደርጉ ነበር። ልክ እንደዚሁ ከሩኩዕ ራሳቸውን ቀና ያደረጉ ጊዜም እጃቸውን ከፍ ያደርጉ ነበር። "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ፣ ረበና ወለከል ሐምድ" ይሉም ነበር። ሱጁድ ላይ ግን ይህንን አያደርጉም ነበር።»

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ አልቡኻሪ - 735

المعنى الإجمالي

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት ውስጥ በሶስት ስፍራዎች በትከሻቸው ትይዩ እጃቸውን ከፍ ያደርጉ ነበር።
የመጀመሪያው ወቅት: የመክፈቻ ተክቢራ ወቅት ሶላትን የጀመሩ ጊዜ ነው።
ሁለተኛው: ለሩኩዕ ተክቢራ ያደረጉ ጊዜ ነው።
ሶስተኛው: ጭንቅላታቸውን ከሩኩዕ ቀና ያደረጉና "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ ረበና ወለከል ሐምድ" ያሉ ጊዜ ነው።
ሱጁድ ማድረግ በሚጀምሩበት ወቅትም ሆነ ከሱጁድ በሚነሱበት ወቅት ግን እጃቸውን ከፍ አያደርጉም ነበር።

من فوائد الحديث

  1. ሶላት ውስጥ እጆችን ከፍ ከማድረግ ጥበቦች መካከል: የሶላት ውበት መሆኑና አላህን ማላቂያ መሆኑ ተጠቃሽ ነው።
  2. ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጅ ከፍ የሚደረግበት አራተኛ ስፍራ መጥቷል። እሱም ከአቡ ሑመይድ አስሳዒዲይ እንደተወራውና አቡዳውድና ሌሎቹም በዘገቡት ሐዲሥ ባለሶስትና ባለአራት ረከዓ ሶላቶች ላይ የመጀመሪያውን ተሸሁድ ብለው (ለሶስተኛው ረከዓ) በሚቆሙበት ወቅት ነው።
  3. በተጨማሪ ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጃቸውን በጆሯቸው ትይዩ ጆሯቸውን ሳይነኩ ከፍ ያደርጉ እንደነበር መጥቷል። ይህም ማሊክ ቢን ሑወይሪሥ ባስተላለፉትና ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲሥ "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ተክቢራ ያደረጉ ጊዜ እጃቸውን በጆሯዋቸው ትይዩ እስኪሆን ድረስ ከፍ ያደርጉት ነበር።"
  4. " ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ" እና "ረበና ለከል ሐምድ" አንድ ላይ የሚለው ኢማምና ብቻውን የሚሰግድ ሰው ብቻ ናቸው። ተከታይ የሆነ ሰው ግን "ረበና ወለከል ሐምድ" ብቻ ነው የሚለው።
  5. ከሩኩዕ በኋላ "ረበና ወለከል ሐምድ" ማለት ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአራት የቃላት ይዘት የመጣ ሲሆን ይህቺም አንዷ ናት። በላጩ ግን አራቱንም የቃላት ይዘት ("ረበና ወለከል ሐምድ" ፤ "አልላሁምመ ረበና ወለከል ሐምድ" ፤ "ረበና ለከል ሐምድ" ፤ "አልላሁምመ ረበና ለከል ሐምድ") በመከታተልና በመሸምደድ አንዳንዴ በዚህ አንዳንዴ በዛ እያቀያየሩ ማለቱ ነው።

عرض الترجمات

58 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
FR Français الفرنسية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
KY Кыргызча القيرقيزية
NE नेपाली النيبالية
YO Yorùbá اليوروبا
LT Lietuvių الليتوانية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
SO Soomaali الصومالية
TG тоҷикӣ الطاجيكية
RW Kinyarwanda الكينياروندا
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
CS Čeština التشيكية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
OM Oromoo الأورومو
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
AZ Azərbaycan الأذربيجانية
UZ O‘zbek الأوزبكية
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية
KMR Kurmancî الكرمنجية