1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

حديث ማለዳ ላይ ወይም ከቀትር በኋላ ወደ መስጂድ የሄደ ሰው ማልዶ በሄደና ከቀትር በኋላ በሄደ ቁጥር አላህ ለርሱ ጀነት ውስጥ መስተንግዶ ያዘጋጅለታል።

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَنْ غَدَا إِلَى الْمَسْجِدِ أَوْ رَاحَ أَعَدَّ اللهُ لَهُ فِي الْجَنَّةِ نُزُلًا، كُلَّمَا غَدَا أَوْ رَاحَ».

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"ማለዳ ላይ ወይም ከቀትር በኋላ ወደ መስጂድ የሄደ ሰው ማልዶ በሄደና ከቀትር በኋላ በሄደ ቁጥር አላህ ለርሱ ጀነት ውስጥ መስተንግዶ ያዘጋጅለታል።"

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ ሙስሊም - 669

المعنى الإجمالي

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለአምልኮም ይሁን ለእውቀት ወይም ከዚህ ውጪ ላሉ መልካም አላማዎች በመጀመሪያው የቀን ክፍልም ሆነ በመጨረሻው የቀን ክፍል በማንኛውም ወቅት መስጂድ የመጣ ሰው በቀኑ ክፍለ ጊዜ ውስጥ ወይም በሌሊቱ ክፍለ ጊዜ ውስጥ መስጂድ በመጣ ቁጥር አላህ ለርሱ ጀነት ውስጥ ስፍራና መስተንግዶ እንዳዘጋጀለት አበሰሩ።

من فوائد الحديث

  1. ወደ መስጂድ የመሄድ ትሩፋትን፣ በመስጂድ ውስጥ በጀመዓ መስገድን በመጠባበቅ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። ከመስጂዶች የሚቀር ሰው ስንትና ስንት ፀጋ፣ ደረጃ፣ ምንዳና አላህ የርሱን ቤት ላሰቡ ያዘጋጀው መስተንግዶ ያመልጠዋል!
  2. ሰዎች ቤቶቻቸው የሚመጣን የሚያከብሩና ለርሱ ምግብ የሚያቀርቡ ከሆነ አላህም ተባረከ ወተዓላ ከፍጡራኑ የበለጠ እጅግ ቸር ነው። የርሱን ቤት ያሰበን ሰው ያከብረዋል፣ አላህ ለርሱም ትልቅና የላቀ መስተንግዶ ያዘጋጅለታል።
  3. ወደ መስጂድ ማልዶም ይሁን አርፍዶ በሄደ ቁጥር ለርሱ መስተንግዶ ስለሚዘጋጅለት ወደ መስጂድ በመሄድ መደሰትና መመኘት ይገባል።

عرض الترجمات

51 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
KY Кыргызча القيرقيزية
NE नेपाली النيبالية
LT Lietuvių الليتوانية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
TG тоҷикӣ الطاجيكية
RW Kinyarwanda الكينياروندا
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
OM Oromoo الأورومو
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية