1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

حديث በእውነተኝነት ላይ አደራችሁን! እውነተኝነት ወደ መልካም ይመራል። መልካም ነገር ደግሞ ወደ ጀነት ይመራልና።

عَنْ عَبْدِ اللهِ بنِ مَسعُودٍ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«عَلَيْكُمْ بِالصِّدْقِ، فَإِنَّ الصِّدْقَ يَهْدِي إِلَى الْبِرِّ، وَإِنَّ الْبِرَّ يَهْدِي إِلَى الْجَنَّةِ، وَمَا يَزَالُ الرَّجُلُ يَصْدُقُ وَيَتَحَرَّى الصِّدْقَ حَتَّى يُكْتَبَ عِنْدَ اللهِ صِدِّيقًا، وَإِيَّاكُمْ وَالْكَذِبَ، فَإِنَّ الْكَذِبَ يَهْدِي إِلَى الْفُجُورِ، وَإِنَّ الْفُجُورَ يَهْدِي إِلَى النَّارِ، وَمَا يَزَالُ الرَّجُلُ يَكْذِبُ وَيَتَحَرَّى الْكَذِبَ حَتَّى يُكْتَبَ عِنْدَ اللهِ كَذَّابًا».

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"በእውነተኝነት ላይ አደራችሁን! እውነተኝነት ወደ መልካም ይመራል። መልካም ነገር ደግሞ ወደ ጀነት ይመራልና። ሰውዬው አላህ ዘንድ እውነተኛ ተብሎ እስኪፃፍ ድረስ እውነት ከመናገርና እውነትን ከመምረጥ አይወገድም። አደራችሁን ውሸትን ተጠንቀቁ! ውሸት ወደ ጥመት ይመራል። ጥመት ደግሞ ወደ እሳት ይመራልና። ሰውዬው አላህ ዘንድ ውሸታም ተብሎ እስኪፃፍ ድረስ ከመዋሸትና ለውሸት ከመጣር አይወገድ።"

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ ሙስሊም - 2607

المعنى الإجمالي

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እውነተኝነትን አዘዙ። እውነተኝነትን አጥብቆ መያዝ ለዘውታሪ መልካም ስራና በመልካም ስራ ላይም እንዲዘወትር የሚያደርገው በመሆኑ ሰውዬውን ወደ ጀነት እንደሚያደርሰው ተናገሩ። ሰውዬው እውነት መናገርን በድብቅም ይሁን በይፋ ከመደጋገም እስካልተወገደ ድረስ እጅግ እውነተኛ የሚል ስያሜ ይሰጠዋል። ይህም በእውነተኝነት ላይ ጫፍ የደረሰ ሰው ማለት ነው። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከውሸትና ከቅጥፈት ንግግር አስጠነቀቁ። ይህም ከቀጥተኛው መንገድ ወደ መጣመም፣ ለክፋትና ለወንጀል ስለሚያነሳሳ ነው። ከዚያም ወደ እሳት ያደርሰዋል። ሰውዬውም ውሸትን ከማብዛት እስካልተወገደ ድረስ አላህ ዘንድ ውሸታም ተብሎ ይፃፋል።

من فوائد الحديث

  1. እውነተኝነት በጥረትና በትግል የሚገኝ የተከበረ ባህሪ ነው። ሰውዬው እውነት የርሱ ባህሪና ተፈጥሮው እስኪሆን ድረስ እውነት ከመናገርና ለእውነትም ከመጣር አይወገድም።
  2. ውሸት ሰውዬው በንግግሩና በተግባሩ በመላመድ ብዛት ባህሪውና መገለጫው እስኪሆንና ቀጥሎም አላህ ዘንድ ከውሸታሞች እስኪፃፍ ድረስ የሚያመጣው የተወገዘ ስነምግባር ነው።
  3. እውነት የሚለው ቃል በምላስ ለሚነገር እውነት ስያሜው ይሰጣል፤ ይህም የውሸት ተቃራኒ ነው። በኒያ ለሚኖር እውነትም ስያሜው ይሰጣል፤ ይህም ስራን ለአላህ ማጥራት (ኢኽላስ) ተብሎ ይጠራል። በነየተው መልካም ነገር ላይ ላለው እውነተኛ ቁርጠኝነትም ስያሜው ይሰጣል። በተግባር ለሚኖር እውነተኝነትም የሚሰጥ ሲሆን ለዚህም ቢያንስ ውስጡና ውጪው እኩል መሆን አለባቸው። ስያሜው በተለያዩ ሁኔታዎች ላይ እውነተኛነትን ለመላበስም ይሰጣል። ለምሳሌ አላህን በመፍራት፣ አላህን በመከጀልና በሌሎችም ሁኔታዎች እውነተኛ መሆንን ሁሉ ያጠቃልላል። በዚህ መልኩ እውነትን የተላበሰ እጅግ እውነተኛ (ሲዲቅ) ይባላል። በተወሰኑት ብቻ እውነተኛ ከሆነ ግን እውነተኛ ብቻ ነው የሚባለው።

عرض الترجمات

52 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
KY Кыргызча القيرقيزية
NE नेपाली النيبالية
LT Lietuvių الليتوانية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
TG тоҷикӣ الطاجيكية
RW Kinyarwanda الكينياروندا
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
CS Čeština التشيكية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
OM Oromoo الأورومو
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
AZ Azərbaycan الأذربيجانية
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية