1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

حديث አንዳችሁ የሚወደውን ህልም በተመለከተ ጊዜ እርሷ ከአላህ ናትና በርሷ ምክንያት አላህን ያመስግንም ለሌሎችም ያውራት፤ ከዚህ ውጪ የሚጠላውን ህልም የተመለከተ ጊዜ ደሞ እርሷ ከሸይጧን ናትና ከክፋቷ በአላህ ይጠበቅ፤ ለአንድም ሰው አያውራ። እርሷም አትጎዳውም።

عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الخُدْرِيِّ رضي الله عنه أَنَّهُ سَمِعَ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«إِذَا رَأَى أَحَدُكُمُ الرُّؤْيَا يُحِبُّهَا فَإِنَّهَا مِنَ اللَّهِ، فَلْيَحْمَدِ اللَّهَ عَلَيْهَا وَلْيُحَدِّثْ بِهَا، وَإِذَا رَأَى غَيْرَ ذَلِكَ مِمَّا يَكْرَهُ، فَإِنَّمَا هِيَ مِنَ الشَّيْطَانِ، فَلْيَسْتَعِذْ مِنْ شَرِّهَا، وَلاَ يَذْكُرْهَا لِأَحَدٍ، فَإِنَّهَا لَنْ تَضُرَّهُ».

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ የአላህ መልዕክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቷል፦
"አንዳችሁ የሚወደውን ህልም በተመለከተ ጊዜ እርሷ ከአላህ ናትና በርሷ ምክንያት አላህን ያመስግንም ለሌሎችም ያውራት፤ ከዚህ ውጪ የሚጠላውን ህልም የተመለከተ ጊዜ ደሞ እርሷ ከሸይጧን ናትና ከክፋቷ በአላህ ይጠበቅ፤ ለአንድም ሰው አያውራ። እርሷም አትጎዳውም።"

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል። ሶሒሕ አልቡኻሪ - 7045

المعنى الإجمالي

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የሚያስደስት መልካም ህልም ማየት ከአላህ እንደሆነ ተናገሩ። በርሱም ላይ አላህን እንዲያመሰግንና ስለርሱም እንዲናገር ጠቆሙ። የሚጠላውንና የሚያሳዝነውን ህልም ያየ ጊዜ ደግሞ ከሸይጧን ነውና ከክፋቱ በአላህ እንዲጠበቅና ለአንድም ሰው እንዳያወራም ጠቆሙ። ህልምን ተከትሎ ከሚመጡ ጎጂ ነገሮች ሰላም ለመሆን ከላይ የተጠቀሰውን ማድረግ አላህ ሰበብ ስላደረገው ምንም አይጎዳውም።

من فوائد الحديث

  1. የህልም ክፍሎች: 1- መልካም ህልም: ይህም እውነተኛ የሆነ ህልምና ለሚያየው ወይም ለታየለት ሰው ከአላህ የሆነ ብስራት ነው። 2- በውስጡ ያወራው: ይህም ሰውዬው በነቃበት ወቅት ለነፍሱ ያወራው ነው። 3- ሸይጧን የአደም ልጆችን ለማሳዘን የሚያሳያቸው የሸይጣን ማሳዘኛ፣ ማስፈራሪያና ማስደንገጫ የሆነ ህልም ነው።
  2. መልካም ህልም ባየ ሰው ዙሪያ የተጠቀሱት ነጥቦች ሶስት ናቸው: አላህን ማመስገን፣ በህልሙ መደሰትና ስላየው ህልም መናገር ናቸው። ነገር ግን የሚናገረው ለሚጠላው ሳይሆን ለሚወደው ሰው ብቻ ነው።
  3. የሚጠላውን ህልም ባየ ሰው አደብ ዙሪያ የተጠቀሱ ነጥቦች አምስት ነገሮች ናቸው: ከህልሙ ክፋትና ከሸይጧን ክፋት በአላህ መጠበቅ፣ ከእንቅልፉ በሚነቃ ጊዜ ወደ ግራው ዞሮ ሶስት ጊዜ መትፋት፣ ከመሰረቱ ለማንም ሰው አለመንገር፣ ወደ መኝታው መመለስ ከፈለገ የነበረበትን ጎን ቀይሮ መዞር ነው። ህልሙም አይጎዳውም።
  4. ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: «መልካም ህልም ሲያይ ለማይወደው ሰው ያለመናገሩ ጥበብ መልካም ህልሙን ለማይወደው ሰው ሲናገር በጥላቻ ወይም በምቀኝነት ምክንያት በማያስደስተው ነገር ይፈታለትና በፈታለት መልኩም ሊከሰት ስለሚችል ነው። ወይም ያ የማይወደው ሰው በሰማው መልካም ህልም ትካዜና ብስጭቱ ሊቻኮልበት ስለሚችል ነው። ስለዚህም በዚህ ምክንያት ለማይወደው ሰው ማውራትን እንዲተው ታዘዘ።»
  5. የአላህ ፀጋዎች በሚከሰቱና ችሮታዎች በሚታደሱ ወቅት ማመስገን እንደሚገባና ይህም እንዲዘወትር ማድረጊያ አንዱ ሰበብ መሆኑን እንረዳለን።

عرض الترجمات

51 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
UG ئۇيغۇرچە الأيغورية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
TA தமிழ் التاميلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
DE Deutsch الألمانية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
SV Svenska السويدية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
NE नेपाली النيبالية
YO Yorùbá اليوروبا
LT Lietuvių الليتوانية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
TG тоҷикӣ الطاجيكية
RW Kinyarwanda الكينياروندا
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
MG Malagasy المالاجاشية
OM Oromoo الأورومو
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
WO Wolof الولوف
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية