عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رَضيَ اللهُ عنهُ أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِنَّ فِي الْجَنَّةِ لَسُوقًا، يَأْتُونَهَا كُلَّ جُمُعَةٍ، فَتَهُبُّ رِيحُ الشَّمَالِ فَتَحْثُو فِي وُجُوهِهِمْ وَثِيَابِهِمْ، فَيَزْدَادُونَ حُسْنًا وَجَمَالًا، فَيَرْجِعُونَ إِلَى أَهْلِيهِمْ وَقَدِ ازْدَادُوا حُسْنًا وَجَمَالًا، فَيَقُولُ لَهُمْ أَهْلُوهُمْ: وَاللهِ لَقَدِ ازْدَدْتُمْ بَعْدَنَا حُسْنًا وَجَمَالًا، فَيَقُولُونَ: وَأَنْتُمْ وَاللهِ لَقَدِ ازْدَدْتُمْ بَعْدَنَا حُسْنًا وَجَمَالًا».

ከአነስ ቢን ማሊክ ረዲየሏሁ ዓንሁ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
«ጀነት ውስጥ (የጀነት ሰዎች) በየጁሙዓው የሚሄዱባት ሱቅ አለች። በስተሰሜን ንፋስ ትነፍስና ፊታቸውንና ልብሳቸውን ትገርፋለች። (በዚህም) ውበትና ቁንጅናን ይጨምራሉ። ውበትና ቁንጅናቸው ጨምሮም ወደ ሚስቶቻቸው ይመለሳሉ። ሚስቶቻቸውም እንዲህ ይሏቸዋል: "በአላህ እንምላለን! ከኛ ከተለያቹ በኋላ ውበትና ቁንጅናችሁ ጨምሯል።" እነርሱም ለሚስቶቻቸው "በአላህ እንምላለን! እናንተም ከኛ ከተለያችሁ በኋላ ውበትና ቁንጅና ጨምራችኋል።"»

ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ ሙስሊም - 2833

المعنى الإجمالي

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ጀነት ውስጥ የጀነት ሰዎች የሚሰባሰቡበትና መሸጥና መግዛት ሳይጠበቅባቸው የፈለጉትን ነገር የሚወስዱበት ቦታ እንዳለ ተናገሩ። ወደዚህም ስፍራ በየሳምንቱ ይመጣሉ። በሰሜን አቅጣጫ ንፋስ ትነፍስና ፊታቸውንና ልብሳቸውን ታንቀሳቅሳለች። በዚህም ውበትና ቁንጅና ይጨምራሉ። ውበትና ቁንጅና ጨምረውም ወደ ሚስቶቻቸው ይመለሳሉ። ሚስቶቻቸውም ለነርሱ እንዲህ ይሏቸዋል: "በአላህ እንምላለን! ከኛ ከተለያችሁ በኋላ ውበትና ቁንጅና ጨምራችኋል።" እነርሱም ለሚስቶቻቸው እንዲህ ይሏቸዋል: "በአላህ እንምላለን! እናንተም ከተለያየን በኋላ ውበትና ቁንጅና ጨምራችኋል።"

من فوائد الحديث

  1. የጀነት ሰዎች ውበትና ቁንጅና እንደሚጨምሩ መገለፁን እንረዳለን።
  2. ሐዲሦቹ የሰው ልጅ ወደዚህች ሀገር የሚዳረስበት ለሆነው መልካም ስራ እንዲጓጓ ያደርጋሉ።
  3. ሐዲሡ ላይ የሰሜን አቅጣጫ ንፋስ ተለይቶ የተጠቀሰው ዐረቦች ዘንድ መልካምንና ዝናብን ይዛ በመምጣት የምትታወቅ ምርጥ ንፋስ ስለሆነች ነው።
  4. ስለጀነትና ፀጋዎቿ በማነሳሳት ወደ አላህ በመጣራት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

عرض الترجمات

40 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
TG тоҷикӣ الطاجيكية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية