1. الرئيسية
  2. التصنيفات
  3. ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

حديث የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሰባት ነገር አዘዙን፤ ከሰባት ነገርም ከለከሉን።

عَنِ الْبَرَاءِ بْنِ عَازِبٍ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ:
أَمَرَنَا رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ بِسَبْعٍ، وَنَهَانَا عَنْ سَبْعٍ: أَمَرَنَا بِعِيَادَةِ الْمَرِيضِ، وَاتِّبَاعِ الْجَنَازَةِ، وَتَشْمِيتِ الْعَاطِسِ، وَإِبْرَارِ الْقَسَمِ، أَوِ الْمُقْسِمِ، وَنَصْرِ الْمَظْلُومِ، وَإِجَابَةِ الدَّاعِي، وَإِفْشَاءِ السَّلَامِ، وَنَهَانَا عَنْ خَوَاتِيمَ -أَوْ عَنْ تَخَتُّمٍ- بِالذَّهَبِ، وَعَنْ شُرْبٍ بِالْفِضَّةِ، وَعَنِ الْمَيَاثِرِ، وَعَنِ الْقَسِّيِّ، وَعَنْ لُبْسِ الْحَرِيرِ وَالْإِسْتَبْرَقِ وَالدِّيبَاجِ.

ከበራእ ቢን ዓዚብ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ:
"የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሰባት ነገር አዘዙን፤ ከሰባት ነገርም ከለከሉን። በሽተኛን በመጠየቅ፣ ጀናዛን በመሸኘት፣ ላስነጠሰ ዱዓ በማድረግ፣ መሃላን ወይም የማለን ሰው በማጥራት፣ ተበዳይን በመርዳት፣ የጠራንን ሰው ጥሪውን በማክበር፣ ሰላምታን በማስፋፋት አዘዙን፤ ከወርቅ ቀለበቶች ወይም የወርቅ ቀለበትን ከመልበስ፣ በብር እቃ ከመጠጣት፣ ከሐር የተሰራ ፎጣ ላይ ከመቀመጥ፣ (አልቀስሲይ) ከሐር ክር ተቀላቅሎ የተሰራን ልብስ ከመልበስ፣ ሐርን ከመልበስ፣ ከወፍራም ሐር የተሰራን ከመልበስ፣ ዲባጅ (ውዱን የሐር ጨርቅ) ከመልበስ ከለከሉን።"

ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል። ሶሒሕ ሙስሊም - 2066

المعنى الإجمالي

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሙስሊሞችን በሰባት ነገሮች አዘዙ፤ ከሰባት ነገሮችም ከለከሏቸው። ያዘዟቸውም ነገሮች: የመጀመሪያው: በሽተኛን መጠየቅ ነው። ሁለተኛው: ጀናዛን መሸኘት፣ በርሱ ላይ መስገድ፣ መቅበርና ለርሱ ዱዓ ማድረግ ነው። ሶስተኛው: ላስነጠሰና አላህን ላመሰገነ ሰው "የርሐሙከሏህ" በማለት ዱዓ እንዲደረግለት ነው። አራተኛው: የማለን ሰው መሃላውን ማጥራትና ማረጋገጥ ነው። ማለትም በአንድ ጉዳይ ቢማልና አንተ መሃላው እውን እንዲሆን ማድረግ ከቻልክ ለመሃላው ማካካሻ ለማውጣት እንዳይገደድ የማለበትን ጉዳይ ፈፅም ማለት ነው። አምስተኛው: የተበደለን ሰው በማገዝ፣ በተቻለ መጠን በርሱ ላይ የሚደርሰውን በደል በመከላከል መርዳት ነው። ስድስተኛው: እንደሰርግ፣ ዐቂቃና ሌሎችም የምግብ ጥሪዎችን ለጠራ ጥሪውን ማክበር ነው። ሰባተኛው: ሰላምታ መስጠትንና ሰላምታን መመለስ ማስፋፋትና ማሰራጨት ነው። የከለከሏቸው ጉዳዮች ደግሞ: የመጀመሪያው: የወርቅ ቀለበት መልበስና በርሱ መዋብ ነው። ሁለተኛው: በብር እቃ መጠጣት ነው። ሶስተኛው: በፈረስና በግመል ኮርቻ ላይ በሚነጠፍ የሐር ፎጣ ላይ መቀመጥ ነው። አራተኛው: (አልቀስሲይ) ከተልባ እግር (ከበፍታ) እና ከሐር ተቀላቅሎ የተሰራን ልብስ መልበስ ነው። አምስተኛው: የሐር ልብስ መልበስ ነው። ስድስተኛው: በወፍራም ሐር የተሰራን ልብስ መልበስ ነው። ሰባተኛው: ዲባጅ መልበስ ነው። እርሱም: ከሐር አይነቶች መካከል ምርጡና ውዱ ነው።

من فوائد الحديث

  1. አንድ ሙስሊም በሙስሊም ወንድሙ ላይ ያሉት ሐቆች መገለፃቸውን እንረዳለን።
  2. በመሰረቱ በሸሪዓ የመጡ ትእዛዛትና ክልከላዎች ባጠቃላይ ወንድን ብቻ እንደሚመለከት ወይም ሴትን ብቻ እንደሚመለከት እስካልመጣ ድረስ ወንዶችንም ሴቶችንም ይመለከታሉ።
  3. ሌሎች ሐዲሦች ሴት ልጅ ጀናዛን ከመሸኘት እንደምትከለከል ይጠቁማሉ።
  4. ሌሎች ሐዲሦች ወርቅና ሐር መልበስ ለሴት ልጅ እንደሚፈቀድ ይጠቁማሉ።

عرض الترجمات

39 اللغة
EN English الإنجليزية
UR اردو الأوردية
ES Español الإسبانية
ID Indonesia الإندونيسية
BN বাংলা البنغالية
TR Türkçe التركية
RU Русский الروسية
BS Bosanski البوسنية
SI සිංහල السنهالية
HI हिन्दी الهندية
ZH 中文 الصينية
FA فارسی الفارسية
VI Tiếng Việt الفيتنامية
TL Tagalog تجالوج
KU Kurdî الكردية
HA Hausa الهوسا
PT Português البرتغالية
ML മലയാളം المليالم
TE తెలుగు التلغو
SW Kiswahili السواحيلية
MY မြန်မာ البورمية
TH ไทย التايلندية
PS پښتو بشتو
AS অসমীয়া الأسامية
SQ Shqip الألبانية
NL Nederlands الهولندية
GU ગુજરાતી الغوجاراتية
PRS دری الدرية
SR Српски الصربية
RO Română الرومانية
HU Magyar المجرية
MOS Moore الموري
KN ಕನ್ನಡ الكانادا
UK Українська الأوكرانية
KA ქართული الجورجية
MK Македонски المقدونية
KM ភាសាខ្មែរ الخميرية
PA ਪੰਜਾਬੀ البنجابية
MR मराठी الماراثية